Loading
Singer
የምትሳሳልኝ የምትወደኝ
ከማንም ይልቅ የምትቀርበኝ
የምትጠብቀኝ ጠዋት ማታ
ጠላቴን በስውር የምትመታ
የምትበቀልልኝ ደም መላሼ
ስምህ ብሩክ ይሁን ወንድም ጋሼ
እናት ሆነህ ጡትክን ያጠባኸኝ
አባት ሆነህ ቀጥተህ ያሳደከኝ
እነደ ታላቅ ወንድም የምትመክረኝ
እንደ እህት ደብቀህ ያጎረስከኝ
ደግሞም ወዳጄ ነህ ሚስጥረኛዬ
የትም የማትለየኝ ጓደኛዬ
የጠላቴ ጠላት ደም መላሼ
ስምህ ብሩክ ይሁን ወንድም ጋሼ
ቁስልህን ስወጋ ሳሳዝንህ
በትቢት እየሄድኩ ሳስቸግርህ
ፊትህ ሲከብድብኝ ስትቆጣኝ
ጅራፍ ስታነሳ ልትቀጣኝ
ወዲያዉ ደግሞ ተንበርክኬ አልቅሼ
ጌታ ማረኝ ስልህ ተመልሼ
በዚያው ክትት አይልም ጨርሶ
እጅህ ይዘረጋል ተመልሶ
አንተ እያለህ መቼ ይበርደኛል
ፀጋህን ስደርብ ይሞቀኛል
ሲርበኝ እግርህ ስር እወድቃለሁ
ፊትህን ሳይ ወዲያው እጠግባለሁ
አዝኜም በፊትህ እደፋለሁ
ቀና ስል በደስታ እሞላለሁ
ምን ልመልስልህ በዚህ ፈንታ
ስምህ ብሩክ ይሁን የኔ ጌታ
እጄ ምንም ሳይኖር ደሃ ሳለሁ
በድህነቴ አንተን አግኝቻለሁ
አላጥላላኸኝም ወደኸኛል
ከነ ግሳን ግሴ አቅፈኸኛል
አሁንም በፀጋህ እቆማለሁ
እስካኖርከኝ ድረስ እኖራለሁ
የሚቆጨው ካለ ይረር እንጂ
እኔ እንደው አልወጣም ካንተ ደጅ
አባት ቢሉህ እናት ቢሉህ ወንድም
ቢሉህ እህት ቢሉህ ወዳጅ ባለንጀራ
ጌታ ሆይ ምን አለ የማትሞላው ስፍራ
የድሃደጎች አባት ነክ አዎ
ለመበለቶችም ዳኛ አዎ
ለታላላቆች ተቆጪ አዎ
ለታናናሾች እረኛ አዎ
የተራቡትን መጋቢ አዎ
የተገፉትን ሰብሳቢ አዎ
ሁሉም አንተው ነህ እራስህ አዎ
ክብር ምስጋና ይድረስህ አዎ