Loading
Singer
አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x) ሀዘንን ፡ በደስታ ፡ ዋይታንም ፡ በሆታ ከስቃይ ፡ ገላግሎ ፡ ሊሞላ ፡ በእፎይታ ታምራቱን ፡ ሊያደርግ ፡ እጅን ፡ በአፍ ፡ ላይ ፡ ሊያስጭን ሊያስብ ፡ ምስኪኖችን አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x) ልጆቹን ፡ ሊያጽናና ፡ ሮሮዋቸውን ፡ ሊያርቅ ችግርን ፡ ሊመታ ፡ ከጭንቀት ፡ ሊያላቅቅ ለጠበቁት ፡ ጸንተው ፡ እርሱን ፡ እርሱን ፡ ላሉት ሲባረኩ ፡ ያያሉ አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x) ወጀቡን ፡ ሊገስጽ ፡ አውሎ ፡ ንፋሱንም ገስግሶ ፡ ሊመጣ ፡ ሳይፈራ ፡ ማንንም የተናጋን ፡ ኑሮ ፡ ሰላም ፡ ሊዘራበት አቤት ፡ ሲችልበት አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x) መከራም ፡ ነገ ፡ ያልፋል ፡ ችግርም ፡ ይረሳል የሚያጠግብ ፡ እንጀራ ፡ በአባት ፡ እጁ ፡ ያጐርሳል በተትረፈረፈ ፣ በሚበቃ ፡ ኑሮ ያኖራል ፡ አክብሮ አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x) እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ እናዝናለን ፡ ላሉ ተዋረድን ፡ አጣን ፡ ተናቅን ፡ ከሰው ፡ ሁሉ ተስፋ ፡ ለቆረጡ ፡ መልካም ፡ ዜና ፡ አለው ይላል ፡ ደርሻለሁ አዝ:- ይመጣል ፣ መልስ ፡ ይዞ ፡ ይመጣል ቀን ፡ ቀጥሯል ፡ ይመጣል ፣ ኑሮን ፡ ያጣፍጣል (፪x)