Loading
Singer
የመከራው ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ አለፈና ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው ፡ አልን ፡ እንደገና ሃሌሉያ ፡ እሰይ ፡ አሜን ፡ አሜን ፡ አልን ኢየሱስን ፡ ይዘን ፡ አሸናፊ ፡ ሆንን (፪x) ከቁጣው ፡ ጢስ ፡ ወጣ ፡ ፍርድ ፡ ከርሱ ፡ በራ አሳትም ፡ ነደደ ፡ ከሰማይ ፡ ወጣና በኪሩቤል ፡ ሆኖ ፡ በፍጥነት ፡ በረረ የጠላቴን ፡ ሰፈር ፡ ገባ ፡ እየሰበረ (፪x) ፍላጻውን ፡ ላከ ፡ ሁሉን ፡ በተናቸው በመብረቁ ፡ እሳት ፡ ጌታ ፡ አወካቸው ቋጠሮውን ፡ ውሉን ፡ ጌታዬ ፡ ፈታታው የፎከረን ፡ ጠላት ፡ መደበቂያ ፡ አሳጣው (፪x) ለወይኔ ፡ አጥር ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ ሆኖ ጠላቴን ፡ በክንዱ ፡ በኃይሉ ፡ በትኖ ይኸው ፡ ለዚህ ፡ እለት ፡ ልንበቃ ፡ ችለናል መከራችን ፡ ሁሉ ፡ እንደጉም ፡ ተነስቷል/በኢየሱስ ፡ ተነስቷል