Loading
የዘላለም ፡ አምላክ ፡ መኖሪያዬ የሕይወቴ ፡ ንጉሥ ፡ አለኝታዬ በከበረው ፡ ደምህ ፡ የቀደስከኝ የመንግሥትህ ፡ ወራሽ ፡ ያረከኝ የኃጢአት ፡ እዳዬን ፡ ከፍለህ መተላለፌንም ፡ ደምስሰህ ማለፍ ፡ ሆኖልኛል ፡ በደምህ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ይሁንልህ አዝ፦ የማይተመን ፡ ነው ፡ በዋጋ ያገኘሁት ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጋ እኔ ፡ አልሄድም ፡ ገፍቼህ ፡ ለፍቅር አይገርመኝም ፡ የቀረው ፡ ይቅር (፪x) መሸ ፡ ነጋ ፡ ሳልል ፡ ዘወትር ቅኔን ፡ እቀኛለሁ ፡ ለአንተ ፡ ክብር ማልጄ ፡ ስነሳ ፡ ምሕረትህ በሌት ፡ አዜማለሁ ፡ እውነትህን ስለ ፡ እኔ ፡ የዋልከው ፡ ውለታ ያረክልኝ ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ተጽፎ ፡ ይኖራል ፡ በልቤ ሊጠፋ ፡ አይችልም ፡ ከሃሳቤ አዝ፦ የማይተመን ፡ ነው ፡ በዋጋ ያገኘሁት ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጋ እኔ ፡ አልሄድም ፡ ገፍቼህ ፡ ለፍቅር አይገርመኝም ፡ የቀረው ፡ ይቅር (፪x) ረክቻለሁ ፡ አርፌያለሁ ረክቻለሁ ፡ ወደኸኛልና ረክቻለሁ ፡ አርፌያለሁ ረክቻለሁ ፡ በልጠህብኛልና አዝ፦ የማይተመን ፡ ነው ፡ በዋጋ ያገኘሁት ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ጋ እኔ ፡ አልሄድም ፡ ገፍቼህ ፡ ለፍቅር አይገርመኝም ፡ የቀረው ፡ ይቅር እኔ ፡ አልሄድም ፡ ገፍቼህ ፡ ለፍቅር አይገርመኝም ፡ የቀረው ፡ ይቅር (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.