Loading
Singer
አባቶች ፡ በእምነት ፡ አምልከውት ፡ አለፉ ነቢያት ፡ አወሩለት ፡ መለከትን ፡ ነፉ ሓዋሪያት ፡ የሰሙት ፡ በዐይናቸው ፡ ያዩት በእጆቻችሀው ፡ ዳሰው ፡ የመሰከሩለት መቃብር ፡ ፈንቅሎ ፡ ሞትን ፡ ድል ፡ የነሳው እርሱን ፡ በማምለኬ ፡ እኔ ፡ እንጓደዳለሁ ከሰማያት ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ያለ በዘምናት ፡ መሃል ፡ እጅግ ፡ የከበረ በሃይል ፡ በችሎቱ ፡ ዝናው ፡ የገነነ በፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ የተመሰገነ ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው ይሄ ፡ ነው ፡ አምላክ ፡ ይሄ ፡ ነው (፪x) እኔ ፡ የማመልከው አዝ፦ የማመልከው ፡ ይህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ የማደንቀው ፡ የምሰግድለት እርሱ ፡ ብቻ ፡ የአማልክት ፡ አምላክ የማመልከው ፡ ይህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ የማደንቀው ፡ የምሰግድለት እግዚአብሔር ፡ የአማልክት ፡ አምላክ ፀሐይን ፡ አቁሞ ፡ ጨረቃን ፡ ያዘገየ አሰራሩ ፡ ልዩ ፡ ከሁሉ ፡ የተለየ ባሕርን ፡ እንደግድግዳ ፡ እንደክምር ፡ ያደረገው የጥንቱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ዛሬም ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው አምላክስ ፡ ካሉ ፡ እንዲህ ፡ ነው መኖር ፡ ካልቀረ ፡ እርሱ ፡ ነው ካመለኩ ፡ አይቀር ፡ እርሱን ፡ ነው አዝ፦ የማመልከው ፡ ይህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ የማደንቀው ፡ የምሰግድለት እርሱ ፡ ብቻ ፡ የአማልክት ፡ አምላክ (፪x) የአህዛብ ፡ አማልክት ፡ ጣኦታቶች ፡ ናቸው አይሰሙ ፡ አያዩ ፡ ቢጠሩ ፡ አይሰሟቸው አምላካቸው ፡ ይቀስቀስ ፡ ተኝቷል ፡ ወይ ፡ ሲባል እኔ ፡ የማመልከው ፡ በእሳት ፡ ይመልሳል የተነሱበትን ፡ ሁሉ ፡ ያደቀቀ በአሸናፊነቱ ፡ ግድሉ ፡ የታወቀ ይሄ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ይሄ ፡ ነው አምላክስ ፡ ካሉ ፡ እንዲህ ፡ ነው መኖር ፡ ካልቀረ ፡ እርሱ ፡ ነው ካመለኩ ፡ አይቀር ፡ እርሱን ፡ ነው አዝ፦ የማመልከው ፡ ይህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ የማደንቀው ፡ የምሰግድለት እርሱ ፡ ብቻ ፡ የአማልክት ፡ አምላክ (፪x)