Loading
Singer
ከሞት ፡ የበረታ ፡ ፍቅሩ ፡ አሽነፈኝ ነፍስም ፡ አልቀረልኝ ፡ ወድጄዋለሁኝ ሰዎች ፡ ሌላም ፡ ቢሉም ፡ ለእኔ ፡ ግን ፡ ፍቅር ፡ ነው ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ብዬ ፡ የማልጠግበው አዝ፦ የማልጠግበው ፡ እኔስ ፡ የማልጠግበው የማልጠግበው ፡ እኔስ ፡ ኢየሱሴን ፡ ነው (፪x) በመልካምነቱ ፡ ደስታን ፡ አጠገበኝ (፪x) ባርኮቱ ፡ በሞላው ፡ ድንኳኑ ፡ ያኖረኝ (፪x) ሥጋት ፡ ቀርቶልኛል ፡ ተደላድያለሁ (፪x) የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ነው ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ያለው (፪x) አዝ፦ ከሰው ፡ ሁሉ ፡ ልዩ ፡ እርሱን ፡ የሚያደርገው ፍቅሩ ፡ ወረት ፡ አያውቅ ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው (፪x) የሚከታተለኝ ፡ በሄድኩበት ፡ ቦታ (፪x) ዐይኖቹ ፡ ዐይነሱም ፡ ከእኔ ፡ ላይ ፡ ለአንድ ፡ አፍታ (፪x) የገባኝ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ እንዲሁ ፡ ወዶኛል (፪x) ፍቅሩም ፡ ከማር ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ ይጣፍጣል (፪x) አዝ፦ ከወይን ፡ ጠጅ ፡ ይልቅ ፡ ፍቅሩ ፡ አጥግቦኛል እኔስ ፡ ሌላ ፡ አልሻም ፡ ኢየሱስ ፡ ይበቃኛል (፪x) ያስደንቀኝ ፡ ጀመረ ፡ እየዋለ ፡ እያደር (፪x) በእኔ ፡ ላይ ፡ የበዛውን ፡ ምህረቱን ፡ ስቆጥር (፪x) ፍቅርና ፡ ምህረቱ ፡ ከቶ ፡ ገደብ ፡ የለው (፪x) ይህን ፡ ኢየሱሴን ፡ ነፍሴ ፡ ወደደችው (፪x) አዝ፦ ከወይን ፡ ጠጅ ፡ ይልቅ ፡ ፍቅሩ ፡ አጥግቦኛል እኔስ ፡ ሌላ ፡ አልሻም ፡ ኢየሱስ ፡ ይበቃኛል (፪x)