Loading
Singer
አዝ፦ የማዕረግ ፡ መዝሙር ፡ እዘምራለሁ ያከበርከኝን ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ ምሥጋናዬን ፡ ጌታ ፡ ተቀበለው አምልኮዬን ፡ ኢየሱስ ፡ ተቀበለው (፪x) በህብህ ፡ ምሥጋናህ ፡ ውስጥ ፡ ትኖራለህና በህዝብህ ፡ አምልኮ ፡ ውስጥ ፡ ትገኛለህና እኔም ፡ አመሰግንሃለሁ ሌላ ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x) አቤቱ ፡ በፈቃድህ ፡ ኃይልን ፡ ሰጥተኸኛል በፊትህም ፡ ደስታ ፡ ደስ ፡ አሰኝተኸኛል ክብሬ ፡ ዝምም ፡ እንዳትል ፡ ትዘምርልሃለች ነፍሴም ፡ ያንተን ፡ ውለታ ፡ ለሁሉ ፡ ታወራለች አዝ፦ የማዕረግ ፡ መዝሙር ፡ እዘምራለሁ ያከበርከኝን ፡ አንተን ፡ አከብራለሁ ምሥጋናዬን ፡ ጌታ ፡ ተቀበለው አምልኮዬን ፡ ኢየሱስ ፡ ተቀበለው (፪x) በህብህ ፡ ምሥጋናህ ፡ ውስጥ ፡ ትኖራለህና በህዝብህ ፡ አምልኮ ፡ ውስጥ ፡ ትገኛለህና እኔም ፡ አመሰግንሃለሁ ሌላ ፡ ሌላማ ፡ ምን ፡ እላለሁ (፪x) በሰው ፡ ልጆች ፡ ሁሉ ፡ ፊት ፡ ለእኔ ፡ ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም ፡ ደግሞ ፡ ሰውረህ ፡ ያስቀመጥካት አቤቱ ፡ ቸርነትህ ፡ እጅግ ፡ በዝታልኛለች የጽድቅንም ፡ ብድራት ፡ አዘጋጅታልኛለች ክብር ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ሞገስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ሞገስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ለሌለህ ፡ አቻ ፤ ለሌለህ ፡ አቻ ለሌለህ ፡ አቻ ፤ ለሌለህ ፡ አቻ (፪x) የሌለህ ፡ ተወዳዳሪ ፡ ግርማህም ፡ እጅግ ፡ አስፈሪ በሠማይና ፡ በምድር ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ የእኛስ ፡ እግዚአብሔር መለወጥ ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ የለም ያው ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም ያው ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም (፪x) ክብር ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ሞገስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው ሞገስ ፡ ለአንተ ፡ ብቻ ለሌለህ ፡ አቻ ፤ ለሌለህ ፡ አቻ ለሌለህ ፡ አቻ ፤ ለሌለህ ፡ አቻ (፪x) ዝቅ ፡ ዝቅ ፡ ብዬ ፡ ከፍ ፡ አደርግሃለሁ በምሥጋና ፡ ዜማ ፡ እቀኝልሃለሁ ከፍ ፡ ካለው ፡ በላይ ፡ ከፍ ፡ ብለሃልና ላመስግንህ ፡ ዛሬ ፡ በአዲስ ፡ ምሥጋና (፪x) ለታላቅነትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለህም (፫x) ለኃያልነትህ ፡ ፍጽማኤ ፡ የለህም (፫x) ለታላቅነትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለህም (፫x) ለኃያልነትህ ፡ ፍጽማኤ ፡ የለህም (፫x) ገናና ፡ ነህ ፡ ብቻህን ፡ ገናና ፡ ነህ ገናና ፡ ነህ ፡ ብቻህን ፡ ገናና ፡ ነህ (፬x)