Loading
Singer
ሊታይ ፡ በማይቻል ፡ ብርሃን ፡ ውስጥ ፡ አለህ ከምድር ፡ ጫፍ ፡ እስከጫፍ ፡ ሁሉ ፡ እኮ ፡ ግዛትህ አለቅነት ፡ ስልጣን ፡ ክብር ፡ የአንተ ፡ ብቻ እናመልክሃለን ፡ ኢየሱስ ፡ የለህ ፡ ብቻ (፪x) አዝ፦ ሃሌሉያ (፪x) ሃሌሉያ ፡ የለህም ፡ እኩያ (፪x) የለህም ፡ እኩያ (፬x) ስግደትና ፡ አምልኮ ፡ ለጌታ ፡ ለሰራዊት ፡ ሁሉ ፡ አለቃ ለሆንከው ፡ አባታችን ፡ ንጉሣችን (ንጉሣችን) ፈዋሻችን ፡ ነህ ፡ አዳኛችን ፡ ምርኩዛችን ፡ መታመኛችን እርስታችን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሃገራችን (ሃገራችን) እንገዛልሃለን ፡ ወድቀን ፡ አዲስ ፡ ቅኔን ፡ እየተቀኘን ክበር ፡ ለዘለዓለም ፡ ንገሥ ፡ ለዘለዓለም ፡ ቅዱስ ፡ አባታችን ሰማይ ፡ ዙፋንህ ፡ ነው ፡ ምድር ፡ መረገጫህ ጊዜና ፡ ሁኔታ ፡ ቦታ ፡ አይወስንህ አሰራርህ ፡ ግሩም ፡ ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው አገዛዝህ ፡ ምቹ ፡ ከማንም ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ሃሌሉያ (፪x) ሃሌሉያ ፡ የለህም ፡ እኩያ (፪x) የለህም ፡ እኩያ (፬x) ስግደትና ፡ አምልኮ ፡ ለጌታ ፡ ለሰራዊት ፡ ሁሉ ፡ አለቃ ለሆንከው ፡ አባታችን ፡ ንጉሣችን (ንጉሣችን) ፈዋሻችን ፡ ነህ ፡ አዳኛችን ፡ ምርኩዛችን ፡ መታመኛችን እርስታችን ፡ እግዚአብሔር ፡ ሃገራችን (ሃገራችን) እንገዛልሃለን ፡ ወድቀን ፡ አዲስ ፡ ቅኔን ፡ እየተቀኘን ክበር ፡ ለዘለዓለም ፡ ንገሥ ፡ ለዘለዓለም ፡ ቅዱስ ፡ አባታችን የጥበብ ፡ ሁሉ ፡ ምንጭ ፡ የዕውቀት ፡ መሰረት የሰላም ፡ የደስታ ፡ የፍቅር ፡ ተምሳሌት አንተ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ለእኛስ ፡ ማረፊያችን እውነተኛ ፡ ወዳጅ ፡ ብሩኩ ፡ ተስፋችን (፪x) አዝ፦ ሃሌሉያ (፪x) ሃሌሉያ ፡ የለህም ፡ እኩያ (፪x) የለህም ፡ እኩያ (፬x)