Loading
Singer
እግዚአብሔርን ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ተስፋ ፡ ያደረኩት ታማኝነቱን ፡ አይቼ ፡ እጄን ፡ ልቤን ፡ የሰጠሁት ያለ ፡ አዋቂዎች ፡ ልቦና ፡ በሰዎች ፡ ተስፋ ፡ ያደርጋል ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ ድህንነትን ፡ ያዘጋጃል አዝ፦ እጅግ ፡ ተቸግሬ ፡ ስማፀን ፡ አይተኸኝ እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እያልከኝ በመጽናናት ፡ ሞልተህ ፡ ደስታን ፡ ታስታጥቀኛለህ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ የዘለዓለም ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ የተማሰው ፡ ጉድጓድ ፡ አፉን ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ አልዘጋም ጉልበቴ ፡ ባለቀ ፡ ጊዜ ፡ ለብቻዬ ፡ አልተውከኝም ስለ ፡ ትንሿ ፡ እምነቴ ፡ ከባለጋራ ፡ ተሟግተህ የድል ፡ አምባ ፡ አስረገጥከኝ ፡ ውጊያውን ፡ ሁሉ ፡ ፈጽመህ አዝ፦ እጅግ ፡ ተቸግሬ ፡ ስማፀን ፡ አይተኸኝ እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እያልከኝ በመጽናናት ፡ ሞልተህ ፡ ደስታን ፡ ታስታጥቀኛለህ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ የዘለዓለም ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ ምሥጋናዬን ፡ እያዜምኩኝ ፡ በአንተ ፡ ደስ ፡ ይለኛል በከንቱ ፡ በሚጠሉኝ ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ አጐናጽፈኸኛል ዓለም ፡ ብትሰርዘኝም ፡ የሕይወት ፡ መዝገብ ፡ አውቆኛል እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ድረስ ፡ ሕይወቴ ፡ በአንተ ፡ ይጸናል አዝ፦ እጅግ ፡ ተቸግሬ ፡ ስማፀን ፡ አይተኸኝ እኔ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ አትፍራ ፡ እያልከኝ በመጽናናት ፡ ሞልተህ ፡ ደስታን ፡ ታስታጥቀኛለህ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ሆይ ፡ የዘለዓለም ፡ ዕድል ፡ ፈንታዬ ፡ ነህ