Loading
Singer
አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x) እንደ ፡ ጥል ፡ ሆንክልኝ ፡ እንደ ፡ አበባ ፡ አበብኩኝ እንደ ፡ ሊባኖስ ፡ ስሬ ፡ በቤትህ ፡ ሥር ፡ ሰደድኩኝ እንደ ፡ ወይራ ፡ ውበት ፡ እንደ ፡ መዓዛዉ በእኔ ፡ ያስቀመጥከው ፡ ዓለምን ፡ ሞላዉ (፪x) አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x) እንደ ፡ ዘንባባ ፡ ዛፍ ፡ እያሳደገኝ ፍሬዬን፡ አበዛው ፡ አለመለመኝ እንደ ፡ ረካች ፡ ገነት ፡ አምላኬ ፡ አደረገኝ በብዛት ፡ በብዛት ፡ በብዛት ፡ ባርኮኝ አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x) እንደ ፡ ጠዋት ፡ ፀሐይ ፡ እንደሚያበራዉ የጻድቃንም ፡ መንገድ ፡ እንደዚሁ ፡ ነዉ ሙሉ ፡ ቀን ፡ እስኪሆን ፡ ገና ፡ ይጨምራል የእኔም ፡ ዕድል ፡ ፈንታ ፡ እነሆ ፡ እንዲህ ፡ ሆኗል አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፪x) በውኑ ፡ ለእግዚአብሔር ፡ የሚሳነው ፡ አለ ፡ ወይ የሥጋ ፡ ለባሽ ፡ አምላክ ፡ የሚያቅተው ፡ አለ ፡ ወይ (፪x) ልቤ ፡ በእግዚአብሔር ፡ ጸና (፬x) እርሱን ፡ ተማመነ ፡ ሆሆ ፡ እርሱን ፡ ተማመነ (፪x) በውሃው ፡ ላይ ፡ እየተረማመደ ፡ እየተረማመደ ለሚፈሩ ፡ እምነትን ፡ አስለመደ (፪x) ማዕበሉም ፡ ወጀቡም ፡ የሚታዘዝለት ይሄ ፡ ማነው ፡ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ የልቤ ፡ አምላክ ፡ የልቤ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ የልቤ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ ፡ ሆሆ (፬x)