Loading
የቀድሞውን ፡ ነገር ፡ አላስብም አሮጌው ፡ ሁሉ ፡ አልፏል ፡ ሁሉ ፡ አልፏል ተፈጠመ ፡ ያየጥንቱ ፡ ታሪክ ፡ ዘመን ፡ መጥቶልኛል የቀድሞውን ፡ ነገር ፡ አላስብም አሮጌው ፡ ሁሉ ፡ አልፏል ፡ ሁሉ ፡ አልፏል የእንባው ፡ ጊዜ ፡ ታሪክ ፡ ሆኖ ፡ ሊቀር ፡ ቀን ፡ ተቀጥሮለታል እነሆ ፡ ሁሉን ፡ አዲስ ፡ አደርጋለሁ እርሱንም ፡ አሁን ፡ አበቅለዋለሁ ያለኝ ፡ ጌታ ፡ ያለኝ ፡ ጌታ የተናገረኝን ፡ ያደርገዋል ፡ ያደርገዋል ፡ አምነዋለሁኝ አምነዋለሁኝ (፬x) ይሆናል ፡ አዲስ ፡ ነገር አያለሁ ፡ አንድም ፡ አይቀር ይሆናል ፡ አዲስ ፡ ነገር አያለሁ ፡ አንድም ፡ አይቀር የተናገረኝ ፡ ጌታ ፡ ሰው ፡ አይደል ፡ ሚያመነታ ቃል ፡ ወጥቷልና ፡ ከእርሱ ፡ ያደርገዋል ፡ ንጉሡ ይሆናል ፡ ይሆናል ፡ ጌታ ፡ ያለው ፡ ይሆናል ይሆናል ፡ ይሆናል ፡ እርሱ ፡ ያለው ፡ ይሆናል (አዲስ ፡ ነገር ፡ ይሆናል ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ አዲስ ፡ ነገር) ሽንፈት ፡ አላወራም ፡ ድል ፡ አለ ፡ ከፊቴ ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ትምክቴ የነሃሱ ፡ ደጃፍ ፡ አውቆ ፡ ይከፈታል እግዚአብሔር ፡ ሲነሳ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ ይቆማል ይሆናል ፡ ይሆናል ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ይሆናል ይሆናል ፡ ይሆናል ፡ እርሱ ፡ ያለው ፡ ይሆናል ዐይኖች ፡ ያላዩትን ፡ ጆሮም ፡ ያልሰማውም ከሰዎች ፡ ዘንድ ፡ ከቶ ፡ ያልተገመተውን እንግዳ ፡ ነገርን ፡ አምላኬ ፡ ያደርጋል አዲስ ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ ይሆናል ቃል ፡ አለኝ ፡ ቃል ፡ አለኝ ፡ እኔ ይሰራል ፡ አያለሁ ፡ በዐይኔ ቃል ፡ አለኝ ፡ ቃል ፡ አለኝ ፡ እኔ ይሰራል ፡ አያለሁ ፡ በዐይኔ አያለሁ ፡ በዐይኔ (፬x) ምድረ ፡ በዳ ፡ ቢሆን ፡ አንተ ፡ ያለህበት አትፍራ ፡ ወንድሜ ፡ ጽና ፡ በቆምክበት ጻድቁ ፡ እግዚአብሔር ፡ እንዴት ፡ ይጥልሃል ታሪክን ፡ ገልብጦ ፡ ገና ፡ ያቆምሃል ተስፋ ፡ የሰጠህ ፡ የታመነው ፡ የታመነው ሁሉን ፡ ይሰራል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ተስፋ ፡ የሰጠህ ፡ የታመነው ፡ የታመነው ሁሉን ፡ ይሰራል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው አምናለሁ ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው ጌታዬ ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው ይሰራል ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው ያደርጋል ፡ እርሱ ፡ ታማኝ ፡ ነው ምድር ፡ ብታልፍ ፡ ሠማይ ፡ ቢያልፍ ቃሌ ፡ ግን ፡ አያልፍም ፡ ያለው ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው (፪x) ኧረ ፡ የምን ፡ ሥጋት ፡ ለምን ፡ ፍርሃት ሁሉን ፡ ቻይ ፡ አምላክ አለኝ ፡ አባት ትዕዛዝ ፡ ከሠማይ ፡ ከአምላኬ ፡ ወጥቶ እንዴት ፡ ይሆናል ፡ አልልም ፡ ከቶ አልልም ፡ ከቶ (፬x) ቃል ፡ አለኝ ፡ ቃል ፡ አለኝ ፡ እኔ ይሰራል ፡ አያለሁ ፡ በዐይኔ ቃል ፡ አለኝ ፡ ቃል ፡ አለኝ ፡ እኔ ይሰራል ፡ አያለሁ ፡ በዐይኔ አያለሁ ፡ በዐይኔ (፬x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.