Loading
Singer
አዝ፦ ማለዳ ፡ አግኝቼው ፡ ቀን ፡ ይናፍቀኛል ቀትር ፡ ላይ ፡ አይቼው ፡ ምሽት ፡ ይርበኛል የሕይወቴ ፡ መመሪያ ፡ ፅኑ ፡ መሠረቴ ትለዋለች ፡ ነፍሴ ፡ ቃልህ ፡ ቁርስ ፡ እራቴ (፪x) ባነበብኩት ፡ ቁጥር ፡ ባሰላሰልኩት በዝቶ ፡ ይበራልኛል ፡ የቃልህ ፡ እውነት ያኔ ፡ ደግሞ ፡ ነፍሴ ፡ ትረሰርሳለች የምድሩን ፡ ረስታ ፡ ወደላይ ፡ ታያለች አሁንም ፡ አሁንም ፡ ስትሻህ ፡ ደጋግማ ልክ ፡ እንደ ፡ ዋላዋ ፡ ቃልህን ፡ ስትጠማ ቢገባት ፡ ነው ፡ ነፍሴ ፡ የቃልህ፡ ውበቱ ጠንካራውን ፡ ልቤን ፡ ማሸነፍ ፡ መርታቱ ተማርኪያለሁ ፡ በቃልህ ፡ ውበት ፡ ተስቢያለሁ ተማርኪያለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ ለእርሱ ፡ ሰጥቻለሁ ተማርኪያለሁ ፡ በቃልህ ፡ ፍቅር ፡ ተይዣለሁ ተማርኪያለሁ ፡ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ፈልገዋለሁ እየኮረኮረ ፡ ገብቶ ፡ ወደ ፡ ሕይወቴ ለውጦ ፡ አስቀረው ፡ የውስጥ ፡ ማንነቴን ልቤም ፡ ተሸነፈ ፡ ተረታ ፡ በቃልህ አምሮ ፡ ተሸላልሞ ፡ ማደሪያህ ፡ ሆነልህ እንዳንበረከከው ፡ ግዛው ፡ ሠልጥንበት በሁለንተናዬ ፡ አንተው ፡ ንገሥበት ይንቆርቆር ፡ በልቤ ፡ ምክር ፡ ተግሳፅህ ሲነጋም ፡ ሲመሽም ፡ ምን ፡ ጊዜም ፡ ልስማህ አዝ፦ ማለዳ ፡ አግኝቼው ፡ ቀን ፡ ይናፍቀኛል ቀትር ፡ ላይ ፡ አይቼው ፡ ምሽት ፡ ይርበኛል የሕይወቴ ፡ መመሪያ ፡ ፅኑ ፡ መሠረቴ ትለዋለች ፡ ነፍሴ ፡ ቃልህ ፡ ቁርስ ፡ እራቴ (፪x) መንፈሴም ፡ ታደሰ ፡ ውስጤ ፡ በረታታ ሲለቀቅ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ቃልህ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ከዓይኔ ፡ ላይ ፡ ተነሳ ፡ ቅርፊቱም ፡ ወደቀ የሕይወቴም ፡ ብርሃን ፡ በቃልህ ፡ ደመቀ ዛሬም ፡ አዲስ ፡ ነገም ፡ ሁሌም ፡ ነው ፡ አዲስ ሲገለጥ ፡ እውነትህ ፡ ለልብ ፡ ለመንፈስ እውነትም ፡ የሕይወት ፡ ቃል ፡ ነህ ፡ መድኃኒቴ አረፈች ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ተጣብቃ ፡ ሕይወቴ ተማርኪያለሁ ፡ በቃልህ ፡ ውበት ፡ ተስቢያለሁ ተማርኪያለሁ ፡ ሕይወቴን ፡ ለእርሱ ፡ ሰጥቻለሁ ተማርኪያለሁ ፡ በቃልህ ፡ ፍቅር ፡ ተይዣለሁ ተማርኪያለሁ ፡ ቶሎ ፡ ቶሎ ፡ ፈልገዋለሁ