Loading
Singer
እኮ ፡ አንተ ፡ የሕይወቴ ፡ መሪ ፡ ነህ አንተ ፡ የሕይወቴ ፡ እረኛ ፡ ነህ ልቤን ፡ ለአንተ ፡ ትቼዋለሁ ዘለዓለም ፡ አምልክሃለሁ (፫x) እውነትን ፡ ልናገር ፡ አይዋሽ ፡ አንደበቴ ውስጤን ፡ ያሳረፈው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ አባቴ ሁሉንም ፡ አስናቀኝ ፡ እኔም ፡ ሁሉን ፡ ተውኩት ጌታዬ ፡ እንደሚሻል ፡ ውስጤን ፡ አሳመንኩት አዝ፦ አለኝ ፡ ልበል እኔ ፡ አለኝ ፡ ልበል አለኝ ፡ ልበል ፡ አባት ውስጤ ፡ ያረፈበት/የኮራበት (፪x) ከሲና ፡ መጣ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ክብር ሕግን ፡ ሊያወጣ ፡ ለዚች ፡ ለምድር በእራሱ ፡ ፈቃድ ፡ የሚጓዘውን ፡ ሕዝብ በእግዚአብሔር ፡ ፀጋ ፡ እንዲተዳደር ካለፈው ፡ ኪዳን ፡ የሚሻል ፡ ኪዳን የእግዚአብሔር ፡ ክብር ፡ ኢየሱስ ፡ መጣ በሰው ፡ ጫንቃ ፡ ላይ ፡ የተቀመጠው ፡ ቀንበር ፡ ተፈታ አዝ፦ አለኝ ፡ ልበል እኮ ፡ አለኝ ፡ ልበል አለኝ ፡ ልበል ፡ አባት ውስጤ ፡ ያረፈበት (፪x) እግዚአብሔር ፡ እረኛዬ ፡ ነው የሚያሳጣኝም ፡ የለም ። በለመለመ ፡ መስክ ፡ ያሳድረኛል በእረፍቱ ፡ ውኃ ፡ ዘንድ ፡ ይመራኛል ። ነፍሴን ፡ መለሳት ስለ ፡ ሥሙም ፡ በፀድቅ ፡ መንገድ ፡ መራኝ ። [1]