Loading
Singer
"በዚያም ፡ በታላቁ ፡ ቀን ፡ ኢየሱስ ፡ ቆሞ 'ማንም ፡ የተጠማ ፡ ቢኖር ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ይምጣና ፡ ይጠጣ በእኔ ፡ የሚያምን ፡ መጽሐፉ ፡ እንዳለው የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ወንዝ ፡ ከሆዱ ፡ ይፈልቃል' ዛሬም ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ ፀሎታችን" የእምነት ፡ ቃሉን ፡ የሰጠ ፡ እስከ ፡ ፍጻሜው ፡ ታማኝ ፡ ነው የፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ አባት ፡ ለልጆቹ ፡ የሚዋጋው እሩህሩህ ፡ አምላኬ ፡ የፍቅር ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ኃጢአት ፡ እንዳይጥለኝ ፡ ያዝከኝ ፡ በቸርነት አዝ፦ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ የነፍስ ፡ ሁሉ ፡ እረኛ ያንቀላፋው ፡ ልቤ ፡ በውሃው ፡ ይነሳል አፍስስ ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስህን ፡ ለተጠማች ፡ ነፍሴ ይፍለቅ ፡ ፍቅርህ ፡ ከሕይወቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ፀሎቴ ማንም ፡ የተጠማ ፡ ቢኖር ፡ ወደኔ ፡ ይምጣ ፡ ብለሃል የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ወንዝ ፡ በሰው ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ ያድራል የመንፈስ ፡ አንደበት ፡ የሰማያት ፡ እንባ ፈሰሰ ፡ ከዓይኔ ፡ መቼም ፡ ላልጠማ አዝ፦ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ የነፍስ ፡ ሁሉ ፡ እረኛ ያንቀላፋው ፡ ልቤ ፡ በውሃው ፡ ይነሳል (ማንም ፡ ለተጠማ ፡ የምትሰጥ ፡ እርካታ) አፍስስ ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስህን ፡ ለተጠማች ፡ ነፍሴ ይፍለቅ ፡ ፍቅርህ ፡ ከሕይወቴ ፡ ይህ ፡ ነው ፡ ፀሎቴ የሕይወት ፡ ውኃ ፡ ምንጭ ፡ በውኃው ፡ ይነሳል አፍስስ ፡ ቅዱስ ፡ መንፈስህን