Loading
Singer
ፍጥረት ሲንከራተት እርካታን ፍለጋ ላይ ታች ሲባዝን ሲል ከቆላ ደጋ አንድ እውነት አለ መፅሃፍ የሚለው እውነትም መንገድም ሕይወትም ኢየሱስ ነው አዝ፦ አንተ የህይወት ቃል አለህ ካንተ ወዴት እሄዳለሁ ካንተ ወደ ማን አያለሁ አማራጬ አይደለህም ብቸኛ መንገዴ ነህ ካንተ ሌላ ካንተ ውጪ እኔ አየሁት ለኔ እንደማይመች አዝ፦ አንተ የህይወት ቃል አለህ ካንተ ወዴት እሄዳለሁ ካንተ ወደ ማን አያለሁ ሥምህን ለሚያምኑ በነፃ የታደለ ሞትን የሚያሸንፍ የሕይወት ቃል አለህ አምነው ለሚድኑ የሕይወት ቃል አለህ መንገድ ነህ ሕይወት ነህ