Loading
Singer
አሃ ፡ አሃ አዝ፦ ለድል ፡ እንጂ ፡ ለሽንፈት ፡ እኔ ፡ አልተጠራሁም (፪x) ጌታዬ ፡ ሲጠራኝ ፡ ከዚያ ፡ ከጨለማ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ እንድረግጥ ፡ ነውና እየሱስ ፡ ሲያወጣኝ ፡ ከዚያ ፡ ከጨለማ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ እንድረግጥ ፡ ነውና በማይመች ፡ ነገር ፡ የሚመቸው ፡ ጌታ ፡ አሃሃ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ስላለ ፡ በድፍረት ፡ እላለሁ ፡ እየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታ (፪x) ድል ፡ አድራጊዉ ፡ ጌታ ፡ ድል ፡ ያንተ ፡ ነዉ ፡ ብሏል ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ድል ፡ መንሳትስ ፡ የታል አሸናፊው ፡ ጌታ ፡ ድል ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ብሏል ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ድል ፡ መንሳትስ ፡ የታል አዝ፦ ለድል ፡ እንጂ ፡ ለሽንፈት ፡ እኔ ፡ አልተጠራሁም (፪x) ጌታዬ ፡ ሲጠራኝ ፡ ከዚያ ፡ ከጨለማ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ እንድረግጥ ፡ ነውና እየሱስ ፡ ሲያወጣኝ ፡ ከዚያ ፡ ከጨለማ እባብና ፡ ጊንጡን ፡ እንድረግጥ ፡ ነውና የምሞትበት ፡ ተሽሯል ፡ አዋጁ ትዕዛዝ ፡ አውጥቷል ፡ ታሪክን ፡ ለዋጩ መስንቆዬም ፡ ይውረድ ፡ ከተሰቀለበት ለአሸናፊው ፡ ጌታ ፡ መዝሙር ፡ ይዜምበት በአዲስ ፡ ምስጋና ፡ በዕልልታ ፡ ሆታ ፊቱ ፡ እገባለሁ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ጌታ ፡ ይኽው ፡ ሽብሸባ ፡ ይኽው ፡ ስግደቴ ድልን ፡ ስለሰጠኝ ፡ ለመድሃኒቴ ለሆነኝ ፡ ጉልበቴ ፡ ይኽው ፡ ስግደቴ ይኽው ፡ እኔነቴ አዝ፦ ይኽው ፡ ተቀበለው ፡ ጌታ ይኽው ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ዕልልታ ይኽው ፡ ተቀበለው ፡ አባ ይኽው ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ጥብጨባ ይኽው ፡ ይኽው ፡ አምልኮው ፡ ይኽው ይኽው ፡ ይኽው ፡ ዝማሬዉ ፡ ይኽው ይኽው ፡ ይኽው ፡ ሽብሸባው ፡ ይኽው ይኽው ፡ ይኽው ፡ ዕልልታው ፡ ይኽው ጨለማዬ ፡ በራ ፡ የፅድቅ ፡ ፀሃይ ፡ ወጣ የመጐብኘት ፡ ዘመን ፡ ይኽው ፡ ለእኔ ፡ መጣ እንዲሁ ፡ አልቀረሁም ፡ በመድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ዘንበለ ፡ ብሎልኛል ፡ ጌታዬ ፡ ከሰማይ ስሙ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ይወደስ ፡ ይግነን የአምልኮ ፡ ሽታ ፡ ቤቱን ፡ የሙላልኝ በጠላቴ ፡ ላይ ፡ ድልን ፡ ለሰጠኝ ፡ ለዚህ ፡ ለጌታ እልልታ ፡ አለኝ ፡ ዝማሬ ፡ አለኝ ሽብሸባ ፡ አለኝ ፡ አምልኮ ፡ አለኝ አዝ፦ ይኽው ፡ ተቀበለው ፡ ጌታ ይኽው ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ዕልልታ ይኽው ፡ ተቀበለው ፡ አባ ይኽው ፡ ላንተ ፡ ያለኝ ፡ ጥብጨባ ይኽው ፡ ይኽው ፡ አምልኮው ፡ ይኽው ይኽው ፡ ይኽው ፡ ዝማሬዉ ፡ ይኽው ይኽው ፡ ይኽው ፡ ሽብሸባው ፡ ይኽው ይኽው ፡ ይኽው ፡ ዕልልታው ፡ ይኽው