Loading
Singer
አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ ታሪኬን ፡ የለወጠው መራራውን ፡ ያጣፈጠልኝ ፤ ሕይወቴን ፡ መልክ ፡ የሰጠው (፪x) እኔስ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እኖርለታለሁ ከኖርኩለት ፡ በላይ ፡ እኖርለታለሁ እኔስ ፡ ለኢየሱሴ ፡ እኖርለታለሁ ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ እሆንለታለሁ ከልካዩ ፡ ከልክሎት ፡ ገድቦት ፡ ነው ፡ እንጂ ሲያስገመግም ፡ መጥቶ ፡ ማዐበሉ ፡ ከደጅ ነገር ፡ ተገልብጦ ፡ መርገሙ ፡ በባርኮት ለሞት ፡ የታጨው ፡ ሰው ፡ በዝቶለታል ፡ ሕይወት አዎ ፡ ልዘምርለት ፤ አዎ ፡ ልቀኝለት አዎ ፡ በእርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ እኔ ፡ ሰው ፡ የሆንኩት ገና ፡ ስለእርሱ ፡ ክብር ፤ ገና ፡ ስለእርሱ ፡ ዝና ገና ፡ እኔ ፡ ዘምሬ ፤ ገና ፡ መች ፡ ጠገብኩና ገና ፡ ከሆንኩት ፡ በላይ ፤ ገና ፡ ብሆን ፡ ሲያንስ ፡ ነው ገና ፡ ያደረገልኝን ፤ ገና ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው በእሳት ፡ ውስጥ ፡ አለፌያለሁ ፡ አላቃጠለኝም በውኃም ፡ አልፌያለሁ ፡ አላሰጠመኝም ምህረቱ ፡ እንደጋሻ ፡ እየከለለኝ የትላንትና ፡ ሃዘኔ ፡ ጌታ ፡ አስረሳኝ ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ልናገር ተመስገን ፡ ከማለት ፡ በቀር እርሱ ፡ ነው ፡ ሰው ፡ ያደረገኝ ትላንትን ፡ እያሻገረኝ ቀን ፡ አለህ ፡ ስለው ፡ ቀን ፡ ሰጠኝ ከቀን ፡ በላይ ፡ ቀን ፡ አሳየኝ ቀን ፡ በቀን ፡ ምህረቱ ፡ በዝቶ አቆመኝ ፡ ቅኔውን ፡ ሞልቶ አዝ፦ ይሄ ፡ ነው ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፤ ታሪኬን ፡ የለወጠው መራራውን ፡ ያጣፈጠልኝ ፤ ሕይወቴን ፡ መልክ ፡ የሰጠው (፪x) እኔስ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ፡ እኖርለታለሁ ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ እሆንለታለሁ እኔስ ፡ ለኢየሱሴ ፡ እኖርለታለሁ ከሆንኩለት ፡ በላይ ፡ እሆንለታለሁ ደመናም ፡ ሳይታይ ፡ ንፋስም ፡ ሳይኖር ሁሉን ፡ ከላይ ፡ አዞ ፡ የሚያሰማምር ጌታ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ ሁሌም ፡ ሁሉን ፡ ቻይ በስራው ፡ ትክክል ፡ የሌለው ፡ ከልካይ አዎ ፡ ልዘምርለት ፤ አዎ ፡ ልቀኝለት አዎ ፡ በእርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ እኔ ፡ ሰው ፡ የሆንኩት ገና ፡ ስለእርሱ ፡ ክብር ፤ ገና ፡ ስለእርሱ ፡ ዝና ገና ፡ እኔ ፡ ዘምሬ ፤ ገና ፡ መች ፡ ጠገብኩና ገና ፡ ከሆንኩት ፡ በላይ ፤ ገና ፡ ብሆን ፡ ሲያንስ ፡ ነው ገና ፡ ያደረገልኝን ፤ ገና ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ የማውቀው ትሞትብኛለህ ፡ አልልም ፡ ሕያው ፡ ነህ ትቀርብኛለህ ፡ አልልም ፡ ቅርቤ ፡ ነህ ትከዳኛለህ ፡ ነህ ፡ አልልም ፡ ታማኝ ፡ ነህ አምላኬ ፡ ከምንም ፡ ከማንም ፡ ልዩ ፡ ነህ ልዩ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ ልዩ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ ልዩ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ (አንተ ፡ ልዩ) ልዩ ፡ ነህ ፡ ኢየሱሴ ፡ ለእኔ ፡ ልዩ ፡ ነህ