Loading
Singer
እጅጉን ፡ ሲራራ ፡ በብዙ ፡ ሲምር ከቶ ፡ ያበቃለትን ፡ የሞት ፡ ፍርድ ፡ ሲሽር ሲስብ ፡ ወደራሱ ፡ ለክብር ፡ መንግስቱ እኔ ፡ እርሱን ፡ የማውቀው ፡ በሰፊ ፡ ትዕግስቱ መክሮ ፡ ሲመልስ ፡ ለክብር ፡ ሲያበቃ ውጦ ፡ ከሚያስቀር ፡ ከረግረጉ ፡ ጭቃ ታሪክ ፡ ቀይሮ ፡ ሥምንም ፡ ሲለውጥ ነጥቆም ፡ ሲታደግ ፡ ካንሸራታቹ ፡ ድጥ (፪x) አዝ፦ይሄ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ይሄ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የምለው ይሄ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ቸር ፡ ያልኩት እግዚአብሔር : እኔ ፡ የወደድኩት (፪x) የተራበው ፡ ሲጠግብ ፡ ሲረካ ፡ ጠጥቶ ሲድን ፡ ከጠላቱ ፡ ወደ ፡ አምላኬ ፡ ሸሽቶ በኖርኩበት ፡ ዘመን ፡ ይሄንን ፡ አውቃለሁ መልካም ፡ ቸር ፡ እረኛ ፡ እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ማነው ከጥላው ፡ በታች ፡ ማረፍ ፡ የወደደ በዓለም ፡ በረሃ ፡ ከስሎ ፡ የነደደ ሸክሙ ፡ ሲራገፍ ፡ እፎይ ፡ ሲል ፡ ሲቀለው በርሱም ፡ ሲታሰብ ፡ ባይኔ ፡ አይቻለሁ (፪x) አዝ፦ይሄ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ይሄ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የምለው ይሄ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ቸር ፡ ያልኩት እግዚአብሔር : እኔ ፡ የወደድኩት (፪x) ክፉኛ ፡ ተወግቶ ፡ ልቡ ፡ ለቆሰለ በኃዘን ፡ ተከቦ ፡ አበቃልኝ ፡ ላለ ወዳጅ ፡ ይሆነዋል ፡ ጌታ ፡ ተጠግቶ ቁስሉን ፡ ያክመዋል ፡ በዘይት ፡ ቀብቶ ቀና ፡ ሲያደርገው ፡ አንገቱን ፡ ላይደፋ የሚጤሰውን ፡ ጧፉን ፡ ሳያጠፋ አትሞትም ፡ በሕይወት ፡ ትኖራለህ ፡ ሲለው የአምላኬን ፡ ፍቅር ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ (፪x) አዝ፦ይሄ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ይሄ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የምለው ይሄ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ቸር ፡ ያልኩት እግዚአብሔር : እኔ ፡ የወደድኩት (፪x) አለኝ ፡ ሊቀ-ካህን ፡ በላይ ፡ በሰማይ አዝኖ ፡ የሚራራ ፡ ድካሜን ፡ የሚያይ ለበደሌ ፡ ስርየት ፡ ለሐጥያቴ ፡ ይቅርታ ሰጠኝ ፡ በምህረቱ ፡ ይሄ ፡ መልካም ፡ ጌታ አባባ ፡ የሚል ፡ የልጅነት ፡ መንፈስ ውስጤ ፡ አፈሰሰ ፡ ቸሩ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ መንፈሱን ፡ ታጥቅኩኝ ፡ ድኛለሁኝ ፡ በቃ ሞትና ፡ እርግማን ፡ ከእንግዲህ ፡ አበቃ አዝ፦ይሄ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ጌታ ይሄ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ የምለው ይሄ ፡ ነው ፡ ደግ ፡ ቸር ፡ ያልኩት እግዚአብሔር፡ : እኔ ፡ የወደድኩት (፬x)