Loading
Singer
ከስምህ ፡ ሌላ ፡ ቀንበር ፡ አይጫነኝ ከፍቅርህ ፡ ሌላ ፡ ዕዳ ፡ አይኑርብኝ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ አግዘኝ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በፍቅርህ ፡ አኑረኝ (፪x) አዝ፦ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ወደጄ ፡ ለአንተ ፡ አስገዛለሁ ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ፈቅጄ ፡ ለአንተ ፡ እኖራለሁ የልቤን ፡ ሃሳብ ፡ መርምረህ ፡ ታውቃለህ አረማመዴን ፡ ትመለከታለህ እግዚአብሔር ፡ ሆይ ፡ ፍፁም ፡ ህግህ ፡ ይግዛኝ የተሰወረ ፡ ኀጢአት ፡ እንዳይገዛኝ (፪x) አዝ፦ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ፈቅጄ ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ወድጄ ፡ ልቤን ፡ አስገዛለሁ ፍቅርህ ፡ ፍፁም ፡ ነው ፡ ነፍስን ፡ ይመልሳል ስራትህ ፡ ልብን ፡ ደስ ፡ ያሰኛል ልጠብቀው ፡ ለቃልህ ፡ እተጋለሁ የዚያን ፡ ጊዜ ፡ ፍፁም ፡ እሆናለሁ (፪x) አዝ፦ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ፈቅጄ ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ፈቅጄ ፡ ወድጄ ፡ ልቤን ፡ አስገዛለሁ ትእዛዝህ ፡ ብሩህ ፡ ዐይንንም ፡ ያበራል ፍራትህ ፡ ንጹህ ፡ ዘላለም ፡ ይኖራል ከከበረ ፡ እንቁ ፡ ይመረጣል ከማር ፡ ይልቅ ፡ እጅግ ፡ ይወደዳል (፪x) አዝ፦ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ወድጄ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ፈቅጄ ፡ ለአንተ ፡ እኖራለሁ ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ወድጄ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ፈቅጂ ፡ ለአንተ ፡ እኖራለሁ ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ፈቅጄ ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ወድጄ ፡ ልቤን ፡ አስገዛለሁ ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ፈቅጄ ፡ ለቃልህ ፡ እገዛለሁ ይኽው ፡ ይኽው ፡ ይኽው ፡ እራሴን ፡ እሰጣለሁ ወድጄ ፡ ልቤን ፡ አስገዛለሁ ይኸው