Loading
Singer
አዝ፦ ይህች ፡ ቀን ፡ ለእኔ ፡ ነች ፡ ጌታ ፡ የሰራት ከሕግ ፡ ባርነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁባት (፪x) አዲስን ፡ ምዕራፍ ፡ በእርሱ ፡ አየሁባት (፪x) ተደላድዬ ፡ በእርሱ ፡ እኖራለሁ ሌሎች ፡ የዘሩትን ፡ እኔ ፡ አጭዳለሁ በተጠናቀቀው ፡ በእሱ ፡ እኖራለሁ አዎ (፬x) ፊደል ፡ ሕይወት ፡ አይሆን ፡ መንፈስ ፡ ካልመጣልኝ በፀጋ ፡ ላይ ፡ ፀጋ ፡ ተትረፈረፈልኝ መውደዱን ፡ ገለጸ ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሞቶልኝ መች ፡ ቃሉን ፡ ያጥፍና ፡ ተናግሮአል ፡ ጌታዬ ኦሆ ፡ ለእኔ (፮x) አዝ፦ ይህች ፡ ቀን ፡ ለእኔ ፡ ነች ፡ ጌታ ፡ የሰራት ከሕግ ፡ ባርነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁባት (፪x) ጌታ ፡ አሳርፎኛል ፡ ስራዬን ፡ ሰርቶልኝ መቅበዝበዜ ፡ አበቃ ፡ ምንም ፡ አልጨምርም አንድም ፡ አላስቀረም ፡ ሁሉን ፡ ፈጽሞልኝ ከክርስቶስ ፡ ጋራ ፡ ወራሽ ፡ አደረገኝ አደረገኝ (፪x) ኦሆ ፡ እኔን ፡ ኦሆሆ ፡ እኔን (፪x) አዝ፦ ይህች ፡ ቀን ፡ ለእኔ ፡ ነች ፡ ጌታ ፡ የሰራት ከሕግ ፡ ባርነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁባት (፪x) ጽድቄ ፡ ከእግዚኣብሔር ፡ ነው ፡ በነጻ ፡ ተሰጥቶኝ ሚኮንነኝ ፡ ማነው ፡ እርሱ ፡ ከወደደኝ ኃጢአት ፡ ተወገደ ፡ በጌታዬ ፡ በኢየሱስ ሞት ፡ መውጊያው ፡ ተቀማ ፡ በሕይወት ፡ እንድነግስ እንድነግስ ኦሆ ፡ እንድነግስ ፡ ኦሆሆ ፡ እንድነግስ (፪x) አዝ፦ ይህች ፡ ቀን ፡ ለእኔ ፡ ነች ፡ ጌታ ፡ የሰራት ከሕግ ፡ ባርነት ፡ ነጻ ፡ ወጣሁባት (፪x)