Loading
ኧረ ፡ ለምን ፡ ይሆን ፡ እንደዚህ የራሴ ፡ እያለኝ ፡ የሰው ፡ የሚያስመኘኝ ያለኝን ፡ አስቶ ፡ ሌላ ፡ የሚያሳየኝ አዝ፦ ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፫x) ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፪x) ምከረው (፪x) ሳለኝ ፡ ብዙ ፡ ምክኒያት ፡ ተመስገን ፡ ምልበት ምነው ፡ ማጉረሜ ፡ ሰነፍ ፡ ይሆንኩበት ያለኝ ፡ ይበቃኛል ፡ ብዬ ፡ እያመሰገንኩ አንተ ፡ በሰጠኸኝ ፡ አንተን ፡ እያከበርኩ ልኑር ፡ እባክህ ፡ እርዳኝ ፡ የሌላ ፡ ሳልመኝ ከበቂ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ አንተ ፡ የሰጠኸኝ ወገኔ ፡ መልካም ፡ ሲሆንለት ምነው ፡ ልቤን ፡ ከፋው ፡ ደስታው ፡ ቅር ፡ አሰኘኝ በመከራው ፡ እኑም ፡ ማመስገን ፡ ተሳነኝ አዝ፦ ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፫x) ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፪x) ምከረው (፪x) ደስ ፡ ካለው ፡ ጋራ ፡ አብሮ ፡ ደስ ፡ ይበለኝ ላዘነውም ፡ ደግሞ ፡ መጽናናት ፡ አድርገኝ በጐ ፡ ህሊና ፡ ስጠኝ ፡ ሃሳቤንም ፡ አቅና የአንተን ፡ ልብ ፡ አርግልኝ ፡ የእኔን ፡ ለውጥና ፍቅርን ፡ ተላብሼ ፡ ትህትናን ፡ ደርቤ ኖሬ ፡ ላስደስትህ ፡ በለኝ ፡ እንደ ፡ ልቤ ያም ፡ ለእኔም ፡ ለእኔ ፡ ምኞቴ እኔና ፡ ለእኔ ፡ ነው ፡ ሁልጊዜ ፡ ፀሎቴ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ለይልኝ ፡ እኔን ፡ ከእኔነቴ አዝ፦ ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፫x) ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፪x) ምከረው (፪x) አንዱ ፡ ሰቀናጣ ፡ ኖሮት ፡ ብዙ ፡ ነገር ሀብቱ ፡ ተትረፍርፎ ፡ ለምርጫ ፡ ሲቸገር ሌላው ፡ ደግሞ ፡ ከፍቶት ፡ የሚበላው ፡ አጥቶ ሲያንቀጠቅጠው ፡ ብርዱ ፡ ውስጡ ፡ ገብቶ ሲፈራረቁበት ፡ ዝናብና ፡ ፀሐይ እያለኝ ፡ ካለፍኩበት ፡ እኔም ፡ ዓይኔ ፡ ሲያይ አዝ፦ ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፫x) ይህ ፡ ልቤን ፡ ተው ፡ በለው (፪x) ምከረው (፪x) ልቤን ፡ ፈውሰው ልቤን ፡ እጠበው ልቤን ፡ ቀይረው ልቤን ፡ ልብ ፡ አርገው (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.