Loading
Singer
የእግዚአብሔር ፡ ምህረቱ ፡ ብዙ ደካሞችንም ፡ ማገዙ በጀርባው ፡ አዝሎ ፡ መሸከሙ ከኃጢአት ፡ ማንጻት ፡ በደሙ (፪x) አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ለዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ (፪x) እኔስ ፡ አይቻለሁኝ ፡ ፍቅሩን ከፋንድያ ፡ ላይ ፡ ማንሳቱን ዛሬ ፡ ሰው ፡ ሆኜ ፡ እዘምራለሁ ለዚህ ፡ ክብር ፡ በቅቻለሁ (፪x) አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ለዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ (፪x) እጅግ ፡ ተንቄ ፡ በሰው ፡ ዘንድ ተጥዬ ፡ ነበር ፡ በአመድ ግን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ፈልጐኝ ከኃጢአት/ከጅግር ፡ ማጥ ፡ ውስጥ ፡ አወጣኝ (፪x) አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ለዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ (፪x) አይገርማችሁም ፡ ወይ ፡ ወገኖች የልዑል ፡ አምላክ ፡ ባሪያዎች ተነሱ ፡ ዘምሩ ፡ ለጌታ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ውለታው (፪x) አዝ፦ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ለዚህ ፡ ያደረስከኝ ፡ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ወይ (፪x)