Loading
Singer
የቱ ፡ ተነግሮ ፡ የቱ ፡ ይተዋል የጌታ ፡ ሥራ ፡ እጅጉን ፡ በዝቷል ከየት ፡ አንስቼ ፡ ስንቱን ፡ ላስታውስ በየማለዳ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ ነግሮ ፡ ሊጨርስ ፡ ማነው ፡ የቻለ ተዓምራቶቹን ፡ እያስተዋለ የጌታን ፡ ክብር ፡ ታላቅነቱን የፍቅሩን ፡ ብዛት ፡ ደግሞ ፡ ጥልቀቱን ከመታወቅም ፡ ሁሉ ፡ ያለፈ ከህሊናችን ፡ ሞልቶ ፡ የተረፈ ነውና ፡ ታላቅ ፡ ሥራው ፡ ብዙ ለዚህ ፡ ለጌታ ፡ ምሥጋናውን ፡ አብዙ ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ፍጥረት ፡ የሚያመሰግንህ ይሄ ፡ ሁሉ ፡ ክብር ፡ ለአንተ ፡ የተገባ ስለሆንክ ፡ ገዢ ፡ ብርቱና ፡ ገናና አሁንም ፡ አሁንም ፡ ይብዛልህ ፡ ምሥጋና ፍጥረታት ፡ በሙሉ ፡ በግዛትህ ፡ ናቸው ስለዚህም ፡ በአንተ ፡ ብዙ ፡ ደስታ ፡ አላቸው በራሳቸው ፡ ቋንቋ ፡ ይመሰክራሉ የእግዚአብሔር ፡ ሥራ ፡ ፍጥረት ፡ ነን ፡ እያሉ ፡ ሃሌሉያ የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ በደማቅ ፡ ብርሃን ፡ እራስክን ፡ ሰውረህ ከፍ ፡ ካሉት ፡ በላይ ፡ እጅግ ፡ ከፍ ፡ ብለህ ድካምና ፡ ዝለት ፡ ሳያውቅህ ፡ እርጅና ትናንትና ፡ ዛሬም ፡ ሁልጊዜ ፡ ገናና ንጉሥ ፡ በንግሥናው ፡ አዋቂው ፡ በዕውቀቱ ሊመስልህ ፡ ሲሞክር ፡ ሲጥር ፡ አይ ፡ ሰው ፡ ከንቱ ነገር ፡ ግን ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ሁሉን ፡ ሲያስተያይ ሁሉን ፡ ብሎ ፡ ያልፋል ፡ የለህም ፡ መሳይ ፡ ሃሌሉያ የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ እግዚአብሔር ፡ እንዲህ ፡ ይህን ፡ ይመስላል ተብሎ ፡ በቃላት ፡ መች ፡ ይገለጻል አንዲያ ፡ ልጁ ፡ በቀኙ ፡ ያለው ተረከው ፡ እንጂ ፡ ሌላ ፡ ማን ፡ አየው ሰማይ ፡ ተቀምጦ ፡ እግሮቹ ፡ ምድር ታላቅነቱ ፡ እንዴት ፡ ይነገር መግለጫ ፡ ቋንቋ ፡ ቢጠፋም ፡ ቃሉ እንዲሁ ፡ ብቻ ፡ ተመሥገን ፡ በሉ የቱ ፡ ተነግሮ ፡ የቱ ፡ ይተዋል የጌታ ፡ ዝና ፡ እጅጉን ፡ በዝቷል ከየት ፡ አንስቼ ፡ ስንቱን ፡ ላስታውስ በየማለዳ ፡ ሁልጊዜ ፡ አዲስ የለህም ፡ መሳይ (፫x) ፡ በምድር ፡ በሰማይ የለህም ፡ እኩያ (፫x) ፡ ኦ ፡ ሃሌሉያ (፪x)