Loading
Singer
የጌታ ፡ የጌታ ፡ ልጅ የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ቀና ፡ በል ፡ እንጂ የአባቴ ፡ የአምላኬ ፡ ልጅ የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ኮራ ፡ በል ፡ እንጂ ጠላት ፡ ሲቆዝም ፡ ያቀርቅር ፡ እንጂ ቀና ፡ ቀና ፡ በል ፡ የጌታ ፡ ልጅ እርሱን ፡ ለፈራው ፡ ላከበረው እስከ ፡ ሺህ ፡ ትውልድ ፡ በረከት ፡ ነው ጌታን ፡ ተማምኖ ፡ የለም ፡ ዝምታ በእርግጥ ፡ ተሰብሯል ፡ ይመለክ ፡ ጌታ ከዚህ ፡ በፊት ፡ የለመድኩት የጠየኩት ፡ ያሳየሁት ፡ ነገር (፪x) ዞሮ ፡ ገባ ፡ እጄ ፡ ገባ አልቀረብኝ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሲናገር ፡ ነገር ዙፋኑ ፡ ስር ፡ መቅደሱ ፡ ስር ማደሪያው ፡ ስር ፡ ስለምነው ፡ ውዬ (፪x) አላፈርኩም ፡ አልከሰርኩም ፡ ተሳካልኝ ፡ ጌታ ፡ ጌታን ፡ ብዬ (፪x) ብዬማ ፡ ጌታ ፡ አለ ፡ ብዬ ብዬማ ፡ ታለምአልኜ ብዬማ ፡ ነገር ፡ ተሳካ ብዬማ ፡ እርሱን ፡ ለምኜ የኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ የበዛባችሁ ቅኔን ፡ ተቀኙለት ፡ እልል ፡ ብላችሁ ለክብሩ ፡ የሚሆን ፡ አምጡ ፡ ምሥጋና እስቲ ፡ ጨምሩለት ፡ ቅዱስ ፡ ነውና ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ የምን ፡ ዝምታ ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ከበሮ ፡ ይመታ ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ሳመልከው ፡ ውዬ ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ሳመልከው ፡ ይነጋ የጌታ ፡ የጌታ ፡ ልጅ የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ቀና ፡ በል ፡ እንጂ የአባቴ ፡ የአምላኬ ፡ ልጅ የኢየሱስ ፡ ልጅ ፡ ኮራ ፡ በል ፡ እንጂ መንግሥተ ፡ ሠማይ ፡ የጀግና ፡ አገር የእኛም ፡ አገር ፡ ነች ፡ በዚያ ፡ እንድንኖር በምድር ፡ መቶ ፡ እጥፍ ፡ በላይ ፡ ደስታ ትልቅ ፡ ዕድል ፡ ነው ፡ መሆን ፡ የጌታ አክሊል ፡ ያገኛል ፡ ድል ፡ ያነሳው ለእግዚአብሔር ፡ ኖሮ ፡ የጨረሰው ኢየሱሴን ፡ ተቀብሎ . (1) . ጌታ ፡ ንጉሥ ፡ ያደረገውን ፡ ሰውን እንደ ፡ እርሱ ፡ የለም ፡ የታደለ ምስጉን ፡ ትውልድ ፡ ከሞት ፡ ያዳነው ፡ ሰው ውኃው ፡ ተባርኮለት ደዌ ፡ ችግር ፡ ተወግዶለት ፡ ሞትን ተዘልሎ ፡ ተቀምጧል እንደ ፡ አንበሳ ፡ አርፏል ፡ በድፍረት ፡ ሕይወት እርሱማ ፡ ያመስግነው እርሱማ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነው እርሱማ ፡ ማቁ ፡ ተቀዶ እርሱማ ፡ ሊዘምረው የኢየሱስ ፡ ውለታው ፡ የበዛባችሁ ቅኔን ፡ ተቀኙለት ፡ እልል ፡ ብላችሁ ለክብሩ ፡ የሚሆን ፡ አምጡ ፡ ምሥጋና እስቲ ፡ ጨምሩለት ፡ ቅዱስ ፡ ነውና ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ የምን ፡ ዝምታ ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ከበሮ ፡ ይመታ ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ሳመልከው ፡ ውዬ ደግሞ ፡ ለጌታ ፡ ሳመልከው ፡ ይነጋ እርሱማ ፡ ያመስግነው እርሱማ ፡ ባለ ፡ ዕዳ ፡ ነው እርሱማ ፡ ማቁ ፡ ተቀዶ እርሱማ ፡ ሊዘምረው