Loading
Singer
አዝ፦ የግሌ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ሙኩሪያ ፡ መመኪያዬ አይቆረቁረኝም ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ ፡ አሃሃ ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ የፀሐዩን ፡ ብርታት ፡ በጥላህ ፡ ከልክለህ ኑሮን ፡ እኖራለሁ ፡ ሳልሳቀቅብህ ፡ አሃሃ ፡ ሳልሳቀቅብህ ለታላቅነትህ ፡ ሲወራ ፡ ሲተረክ ቃላቶች ፡ አቅም ፡ አጠራቸው ፡ ለመግለጽ ከሰማያት ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ከምድርም ፡ በታች ፡ በታች ፡ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ እንደ ፡ ገለፅክልን ፡ ሥምህን ፡ ልባርክህ (፪x) አዝ፦ የግሌ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ሙኩሪያ ፡ መመኪያዬ አይቆረቁረኝም ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ ፡ አሃሃ ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ የፀሐዩን ፡ ብርታት ፡ በጥላህ ፡ ከልክለህ ኑሮን ፡ እኖራለሁ ፡ ሳልሳቀቅብህ ፡ አሃሃ ፡ ሳልሳቀቅብህ አትታማም ፡ ክፉ ፡ አድርገሃል ፡ ተብለህ ለልጆችህ ፡ ሁሌ ፡ መልካም ፡ ነህ ከማደሪያህ ፡ ቃል ፡ ትልካለህ የዛለን ፡ ልብ ፡ ታሳርፋለህ አምላክ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (፪x) ንጉሥ ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (፪x) ኃያል ፡ ነህ ፡ ጌታዬ (፫x) አዝ፦ የግሌ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ሙኩሪያ ፡ መመኪያዬ አይቆረቁረኝም ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ ፡ አሃሃ ፡ ትከሻህ ፡ ጌታዬ የፀሐዩን ፡ ብርታት ፡ በጥላህ ፡ ከልክለህ ኑሮን ፡ እኖራለሁ ፡ ሳልሳቀቅብህ ፡ አሃሃ ፡ ሳልሳቀቅብህ