Loading
Singer
የጌታዎች ፡ ጌታ ፡ የነገሥታት ፡ ንጉሥ የይሁድ ፡ አንበሳ ፡ የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ በአምባ ፡ ላይ ፡ ፈረስ ፡ የምትቀመጠው በክብር ፡ በግርማ ፡ የምትመለሰው የዘለዓለም ፡ ተስፋችን ፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ የደህንነታችን ራስ አዝ፦ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ ፊትህ ፡ እንደፀሐይ ፡ በሃይል ፡ ያበራል ፍቅርህ ፡ ከዕንቁ ፡ ይልቅ ፡ ልብን ፡ ይማርካል ውበትህ ፡ ያማረ ፡ ክብርህን ፡ ተላብሰሃል ተመስገን ፡ ጌታችን ፡ ተባረክ ፡ ብለናል በምድር ፡ ክብር ፡ በሠማይ ይገባሃልና ፡ መንገሥ ፡ ከሁሉም ፡ በላይ አዝ፦ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ ብዙዎች ፡ ተገዙ ፡ ፍቅርህን ፡ ተረድተው እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያላ ፡ ማንም ፡ የለም ፡ ብለው ድምጻቸው ፡ ተሰማ ፡ ከየማዕዘኑ ቅኔን ፡ ተቀኙልህ ፡ በስምህ ፡ የዳኑ ተመስገን ፡ ተባረክ ፡ ብለው ዘምረው ፡ አይጠግቡም ፡ ደስታህ ፡ ኃይላቸው ፡ ነው አዝ፦ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ ይገባሃልና (፫x) ፡ ኦሆ