Loading
Singer
Updated 3d ago
ከሚያመልኩ ፡ ጋራ ፡ ከሚያነግሱህ ፡ ጋራ እኔም ፡ ተስማምቼ ፡ ላንግስህ ፡ ማዳንህን ፡ ላውራ ፊትህ ፡ ከሚሰግዱ ፡ በቅኔ ፡ ዝማሬ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ አሜን ፡ ልበል እኔም ፡ ተጨምሬ ፡ ላንግስህ ፡ እኔም ፡ ተጨምሬ እኔም ፡ ተደምሬ ፡ ላምልክህ ፡ ኢኸው ፡ ለአንተ ፡ ክብሬ ከመስዋዕት ፡ ይልቅ ፡ ምሥጋናን ፡ ወደሃል ፡ አህህ በእውነት ፡ በመንፈስ ፡ አምልኮ ፡ ከብረሃል እንደዳዊት ፡ ጥሎ ፡ ማንነት ፡ ክብሩን ፡ አህህ የሚዘልልህን ፡ ወደድከው ፡ ያንን ፡ አህህ አዝ፦ ይገባሃል (፫x) ፡ ከዚህ ፡ በላይ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ አልተገኘምና ፡ አንተን ፡ መሳይ (፪x) አምላክ ፡ በመቅደሱ ፡ ኪሩቤል ፡ ላይ ፡ ሆኖ ፡ አህህ በረጅም ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ገኖ ፡ አህህ ማደሪያውን ፡ ከበው ፡ ያሉት ፡ መላዕክት ፡ አህህ አንዱም ፡ ለአንዱ ፡ ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ ነህ ፡ ሲሉት ፡ አህህ አዝ፦ ይገባሃል (፫x) ፡ ከዚህ ፡ በላይ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ አልተገኘምና ፡ አንተን ፡ መሳይ (፪x) ከሚያመልኩ ፡ ጋራ ፡ ከሚያነግሱህ ፡ ጋራ እኔም ፡ ተስማምቼ ፡ ላንግስህ ፡ ማዳንህን ፡ ላውራ ፊትህ ፡ ከሚሰግዱ ፡ በቅኔ ፡ ዝማሬ ከእነርሱ ፡ ጋር ፡ አሜን ፡ ልበል እኔም ፡ ተጨምሬ ፡ ላንግስህ ፡ እኔም ፡ ተጨምሬ እኔም ፡ ተደምሬ ፡ ላምልክህ ፡ ኢኸው ፡ ለአንተ ፡ ክብሬ ቀን ፡ ለቀን ፡ ሌሊትም ፡ ለሌሊት ፡ ሲያወጉ በቋንቋቸው ፡ የእርሱን ፡ ክብር ፡ ሲተርኩ ጨረቃና ፡ ፀሐይ ፡ እያብረቀረቁ እግዚአብሔር ፡ ሰራን ፡ ሲሉ ፡ እያደነቁ አዝ፦ ይገባሃል (፫x) ፡ ከዚህ ፡ በላይ በሰማይም ፡ በምድርም ፡ አልተገኘምና ፡ አንተን ፡ መሳይ (፪x)