Loading
Singer
በሰልፉ ፡ ሜዳ ፡ በዝቶ ፡ ጠላቴ ፍርሃት ፡ ሲያርደኝ ፡ ፈርቶ ፡ ጉልበቴ ጠፍሁ ፡ ብዬ ፡ ስል ፡ ወየው ፡ ጌታዬ ከፊቴ ፡ ያልፋል ፡ ኢየሱስ ፡ ጋሻዬ አዝ፦ ካፈጠጠብኝ ፡ በዓለም ፡ ካለዉ እጅግ ፡ ይበልጣል ፡ በእኔ ፡ ያለው የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ ተቆጣጣሪው ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ጠላት ፡ እንደ ፡ ንብ ፡ ከቦኝ ፡ ቢመጣ ምሽጌን ፡ ትቼ ፡ እኔም ፡ አልወጣም በእግዚአብሔር ፡ ሥም ፡ እሸንፋለሁ ጐልያድም ፡ ወድቆ ፡ በዓይኔ ፡ አየዋለሁ አዝ፦ ካፈጠጠብኝ ፡ በዓለም ፡ ካለዉ እጅግ ፡ ይበልጣል ፡ በእኔ ፡ ያለው የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ ተቆጣጣሪው ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ፅኑ ፡ ኃያሉ ፡ የአምላክ ፡ ጦረኛ አንዱ ፡ ለሺህ ፡ ነው ፡ የእምነት ፡ አርበኛ ከአመፀኞች ፡ እጅ ፡ ደሙን ፡ በትኖ ፍሬውን ፡ ያበዛል ፡ በአምላኩ ፡ ታምኖ አዝ፦ ካፈጠጠብኝ ፡ በዓለም ፡ ካለዉ እጅግ ፡ ይበልጣል ፡ በእኔ ፡ ያለው የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ ተቆጣጣሪው ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ረዳት ፡ እንዳለኝ ፡ ጠላቴም ፡ ያያል እንደ ፡ ዘበተ ፡ መቼ ፡ ይቀራል የመስቀል ፡ ፅዋ ፡ እኔም ፡ ጠጣለሁ ድል ፡ ይታወጃል ፡ አሻገራለሁ አዝ፦ ካፈጠጠብኝ ፡ በዓለም ፡ ካለዉ እጅግ ፡ ይበልጣል ፡ በእኔ ፡ ያለው የፍጥረት ፡ ገዢ ፡ ተቆጣጣሪው ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው (፪x)