Loading
Singer
አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ የያዘው ፡ ነገር እንዳይወድቅ ፡ አይፈራ ፡ እንዳይጠፋ ፡ አይፈራ ከጥላው ፡ ሥር ፡ ያረፈው ፡ ሰው ዘላለሙ ፡ አያሰጋው (፪x) አባትዬ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ (፪x) ኑሮዬ ፡ በአንተ ፡ እጅ (፪x) አባትዬ ፡ የእኔ ፡ ከለላ ፡ ከለላዬ በጥላህ ፡ ሥር ፡ ነው ፡ ማደሪያዬ (፪x) በእናቴ ፡ ማህፀን ፡ ደም ፡ ሳለሁኝ ፡ አጥንቶቼም ፡ ሳይዋደዱ አንተው ፡ ታውቀው ፡ ነበር ፡ እንዲህ ፡ እንዲሆን ፡ የሕይወቴ ፡ አካሄዱ ደግሞስ ፡ ካሳለፍከኝ ፡ በቸርነትህ ፡ የትላንቱን ፡ ጨለማ ለነገውስ ፡ ቢሆን ፡ ለምን ፡ አላምንም ፡ ሕይወቴ ፡ በእጅህ ፡ ነውና ተውኩት ፡ ሁሉንም ፡ ለአንተ ፡ ተውኩት ተይ ፡ ነፍሴ ፡ እኔ ፡ አላውቅም ፡ ብዬ ፡ እንዳልኩት ይሁን ፡ ያልከው ፡ የፀና ፡ ለመሆኑ ምስክር ፡ ነው ፡ ሰማይ ፡ የለ ማዕገር መቆሙ አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ የያዘው ፡ ነገር እንዳይወድቅ ፡ አይፈራ ፡ እንዳይጠፋ ፡ አይፈራ ከጥላው ፡ ሥር ፡ ያረፈው ፡ ሰው ዘላለሙ ፡ አያሰጋው (፪x) አባትዬ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ (፪x) ኑሮዬ ፡ በአንተ ፡ እጅ (፪x) አባትዬ ፡ የእኔ ፡ ከለላ ፡ ከለላዬ በጥላህ ፡ ሥር ፡ ነው ፡ ማደሪያዬ (፪x) ክብርን ፡ የምትገልፅበት ፡ ደካማ ፡ ሰው ፡ ስትፈልግ ፡ አገኘኸኝ እንጂማ ፡ በእራሴ ፡ እንኳን ፡ በአንተ ፡ በሰውም ፡ ዓይን ፡ የማልሞላ ፡ ነኝ ግና ፡ ከወደድከኝ ፡ በዓይነህ ፡ ከታየሁ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ እልሃለሁ አንተ ፡ ነህ ፡ ደጀኔ ፡ ተባረክልኝ ፡ ከትከሻህ ፡ የሚያወርደኝ ፡ ማነው አልጥልሽ ፡ አልተውሽ ፡ እያልክ ልቤን ፡ ስትደግፈኝ ፡ እንደዋልክ አይቼህ ፡ መንፈሴ ፡ ረካ አትተወኝም ፡ አትረሳኝም ፡ ለካ አዬ ፡ አትረሳኝም ፡ ለካ አትተወኝም ፡ በቃ ፡ አትረሳኝም ፡ በቃ አሄ ፡ አትረሳኝም ፡ በቃ አትተወኝም ፡ በቃ ፡ አትለቀኝም ፡ በቃ አሄ ፡ አትለቀኝም ፡ በቃ (፪x)