Loading
Singer
እኔስ ፡ በአምላኬ ፡ በጌቶች ፡ ጌታ ይህ ፡ ነው ፡ አይባልም ፡ ያለኝ ፡ ደስታ ደመና ፡ ሳይኖር ፡ በአካባቢዬ ግራ ፡ ተጋብቷል ፡ ጠላት ፡ በደስታዬ (፫x) አዝ፦ የደስታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከውስጤ ፡ ወስዶ አመልከዋለሁ ፡ ከጠዋት ፡ ማታ ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ደስታ ፡ (ጌታ) (፬x) የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖ ሃዘኔ ፡ ጠፋ ፡ እንደጉም ፡ በንኖ አላማርርም ፡ አላንጐራጉር ደስተኛ ፡ ነኝ ፡ ሁሌ ፡ በእግዚአብሔር (፫x) አዝ፦ የደስታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከውስጤ ፡ ወስዶ አመልከዋለሁ ፡ ከጠዋት ፡ ማታ ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ደስታ ፡ (ጌታ) (፬x) ማን ፡ ደስ ፡ ሊለው ፡ እኔ ፡ ልከፋ በትንሽ ፡ ትልቁ ፡ ደስታዬ ፡ አይጠፋ ለጠላት ፡ ወሬ ፡ ጆሮም ፡ አልሰጠው ደስታዬ ፡ ፍጹም ፡ መቼም ፡ ማይወሰድ ፡ ነው (፫x) አዝ፦ የደስታ ፡ መንፈስ ፡ በላዬ ፡ ወርዶ ሃዘን ፡ ምሬቴን ፡ ከውስጤ ፡ ወስዶ አመልከዋለሁ ፡ ከጠዋት ፡ ማታ ኢየሱስ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የኔ ፡ ደስታ ፡ (ጌታ) (፬x)