Loading
Singer
የሕይወቴ ፡ እረኛ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ ፡ የማይተኛ (፪x) የሕይወቴ ፡ ጠበቃ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እንዳልሰጋ (፪x) እኔማ ፡ ዕድለኛ ፡ ነኝ አልፈራም ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ ዓለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ አይወድቅም ፡ በንፋስ ፡ ቤቴ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ተዋድጄ ይፈልቃል ፡ ሰላም ፡ ከደጄ ለካ ፡ ለካ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው (፪x) የትላንቱን ፡ ያንን ፡ ወጀብ ፡ ፀጥ ፡ ያረገው (፪x) ኧረ ፡ እኔ አመል ፡ ሆኖብኛል ፡ አመል (፪x) ስነሳ ፡ ስቀመጥ ፡ ለክብርህ ፡ መዘመር እንደዚህ ፡ ካልሆነ ፡ ይደክመኛል ፡ መኖር የእኔ ፡ ነህ (፪x) የእኔ ፡ ነህ ፡ ብልህ ከመሞት/ከጭንቀት ፡ ያዳንከኝ ጌታዬ ፡ እኮ ፡ ነህ (፪x) ከእንግዲህማ ፡ ወዳጅ ፡ አግኝቻለሁ ከእንግዲህማ ፡ አብሮ ፡ የሚዘልቅ ከእንግዲህማ ፡ እንዲህ ፡ ከወደደ ከእንግዲህማ ፡ ጥሎ ፡ የማይሄድ (፪x) የሕይወቴ ፡ እረኛ ፡ ጌታ ፡ አለልኝ ፡ የማይተኛ (፪x) የሕይወቴ ፡ ጠበቃ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ እንዳልሰጋ (፪x) እኔማ ፡ ዕድለኛ ፡ ነኝ አልፈራም ፡ ጌታ ፡ ስላለኝ ዓለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ አይወድቅም ፡ በንፋስ ፡ ቤቴ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ተዋድጄ ይፈልቃል ፡ ሰላም ፡ ከደጄ ለካ ፡ ለካ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው (፪x) የትላንቱን ፡ ያንን ፡ ወጀብ ፡ ፀጥ ፡ ያረገው (፪x)