Loading
Singer
የዳዊት ፡ የአብርሃም ፡ ልጅ ፡ ያሉት ነብያት ፡ ቀድመው ፡ የተረኩት በድንግል ፡ በማርያም ፡ ያደረ የትውልድ ፡ ሐረግ ፡ ያስቆጠረ ልደቱ ፡ በቤተልሔም በንጉሥ ፡ በሄሮድስ ፡ ዘመን እረኞች ፡ በግርግም ፡ ያዩት ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ መድኃኒት የይሁዳ ፡ ምድር ፡ አንቺ ፡ ቤተልሔም ከይሁዳ ፡ ግዛቶች ፡ ከቶ ፡ አታንሺም እስራኤልን ፡ የሚጠብቅ ፡ መስፍን ፡ ካንቺ ፡ ይወጣል ተብሎ ፡ እንደተነገረ ፡ ኢየሱስ ፡ ተወልዷል መልአኩ ፡ ወደ ፡ ማርያም ፡ ገብቶ የሰላም ፡ ድምጹን ፡ አሰምቶ አምላኬ ፡ ፀጋ ፡ የሞላብሽ ማርያም ፡ ሆይ ፡ በይ ፡ ደስ ፡ ይበልሽ እነሆ ፡ ልጅን ፡ ትወልጃለሽ ሥሙንም ፡ ኢየሱስ ፡ ትይዋለሽ በያዕቆብ ፡ ቤት ፡ ሁሉ ፡ ይነግሳል የእግዚአብሔር ፡ ልጅ ፡ እርሱም ፡ ይባላል ነፍሴ ፡ ጌታን ፡ ትባርከው ፡ መንፈሴም ፡ አምላኬን ውርደቴን ፡ ተመልክቷል ፡ የባሪያይቱን ብርቱ ፡ የሆነው ፡ እርሱ ፡ በእኔ ፡ ክብሩን ፡ ገልጧል ትዕቢተኛን ፡ አዋርዶ ፡ ትሁቱን ፡ አክብሯል ቃል ፡ ነበር ፡ ቃልም ፡ እግዚአብሔር ይህም ፡ ቃል ፡ በአብ ፡ ዘንድ ፡ ነበር በእርሱ ፡ ሕይወት ፡ ትኖራለች ሕይወትም ፡ የሰው ፡ ብርሃን ፡ ነች ከሆነው ፡ አንዳች ፡ አለእርሱ አልሆነም ፡ ሁሉ ፡ ሆነ ፡ በርሱ ዓለምን ፡ ያጸናበት ፡ ቃሉ እነሆ ፡ ለሚያምኑበት ፡ ሁሉ ቃልም ፡ ሥጋ ፡ ሆነና ፡ ፀጋን ፡ እውነት ፡ ተሞልቶ በእኛ ፡ ዘንድ ፡ አደረ ፡ ክብሩን ፡ አየን ፡ ጐልቶ በአባቱ ፡ እቅፍ ፡ ሆኖ ፡ አብን ፡ የተረከው ቀድሞም ፡ የነበረው ፡ ቃል ፡ ወልድ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው