Loading
Singer
ሳልጠራጠር ፡ ሁሉን ፡ ቻይነቱን አመልከዋለሁ ፡ እያየሁ ፡ ጉልበቱን/ሞገሱን ሳልጠራጠር ፡ ሁሉን ፡ ቻይነቱን አመልከዋለሁ ፡ እያየሁ ፡ ብርታቱን/ችሎቱን (፪x) የእኔ/የእኛ ፡ ጌታ ፡ ሁሉንም ፡ ይችላል እስኪ ፡ የቱ ፡ ምንስ ፡ አቅቶታል የእኔ/የእኛ ፡ ጌታ ፡ ሁሉንም ፡ ይችላል ኧረ ፡ የቱ ፡ ምንስ ፡ አቅቶታል (፪x) ግዙፉን ፡ ተራራ ፡ ማደላደል ፡ ነው ፡ ዎይ (እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል) ጥልቁን ፡ ሸለቆ ፡ ውሃ ፡ መሙላት ፡ ነው ፡ ዎይ (እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል) የተዘጋውን ፡ ደጅ ፡ መከፋፈት ፡ ነው ፡ ዎይ (እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል) ለጨለመው ፡ ሕይወት ፡ ብርሃን ፡ መስጠት ፡ ነው ፡ ዎይ (እግዚአብሔር ፡ ይህንን ፡ ይችላል) ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ እርሱ ፡ ይችላል ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ ጌታ ፡ ይችላል ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ በደንብ ፡ ይችላል ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ ጌታ ፡ ይችላል አንሱ ፡ ካለ ፡ ማንሳት ፡ እንጂ ፡ ድንጋዩን መከራከር ፡ መሟገቱ ፡ ለምን ሕያው ፡ ይሁን ፡ ይፈታ ፡ እንጂ ፡ አልዓዛር ከሰው ፡ እኩል ፡ ይቁም ፡ ይብቃ ፡ ለክብር ሁሉን ፡ ቻዩ ፡ ተናገረ ፡ ቃል ፡ አወጣ እስከመቼ ፡ ያለማመን ፡ ብሎ ፡ ጣጣ የማይሆነውን ፡ የሚያደርግ ፡ እንዲሆን ያለረዳት ፡ ያለአጋዥ ፡ ብቻውን ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለእርሱ ፡ ብቻ ፡ ለእግዚአብሔር (፫x) ሳልጠራጠር ፡ ሁሉን ፡ ቻይነቱን አመልከዋለሁ ፡ እያየሁ ፡ ጉልበቱን/ሞገሱን ሳልጠራጠር ፡ ሁሉን ፡ ቻይነቱን አመልከዋለሁ ፡ እያየሁ ፡ ብርታቱን/ችሎቱን (፪x) የእኔ/የእኛ ፡ ጌታ ፡ ሁሉንም ፡ ይችላል እስኪ ፡ የቱ ፡ ምንስ ፡ አቅቶታል የእኔ/የእኛ ፡ ጌታ ፡ ሁሉንም ፡ ይችላል ኧረ ፡ የቱ ፡ ምንስ ፡ አቅቶታል (፪x) የሞተውን ፡ ተነስ ፡ ውጣ ፡ ማለት ፡ ነው ፡ ዎይ (እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል) የታሰረውን ፡ ሰው ፡ ፈትቶ ፡ መልቀቅ ፡ ነው ፡ ዎይ (እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል) እንቆቅልሽ ፡ ፍቺ ፡ መልስ ፡ መስጠት ፡ ነው ፡ ዎይ (እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል) የጠላትን ፡ ሃሳብ ፡ ማፈራረስ ፡ ነው ፡ ዎይ (እግዚአብሔር፡ ይህንን ፡ ይችላል) ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ እርሱ ፡ ይችላል ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ ጌታ ፡ ይችላል ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ በደንብ ፡ ይችላል ይችላል ፡ ይችላል ፥ ይችላል ፡ ጌታ ፡ ይችላል