Loading
Singer
ይችላል /4/ ድንቅና ታምራት ብቻውን ያደርጋል ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሄር ይቻላል ሃኪም ያቃተውን ደዌ ይፈውሳል - እግዚአብሔር ይችላል ህዝብን ያናወጠን ማዕበል ይገስፃል - እግዚአብሔር ይችላል እርኩስ መንፈስ ፊቱ መች ችሎ ይቆማል - እግዚአብሔር ይችላል ለኢየሱስ ክብር ወድቆ ይንበረከካል - እግዚአብሔር ይችላል ይችላል /2/ እግዚአብሄር ይችላል ድንቅና ታምራት ብቻውን ያደርጋል ድንቅና ታምራት ብቻውን ያደርጋል ለሰው የማይቻል ለእግዚአብሄር ይቻላል ነፋስን ይጠራል ባህር ዝም ያሰኛል - እግዚአብሔር ይችላል የተፍገመገመን አፅንቶ ያቆማል - እግዚአብሔር ይችላል አለትን ሰንጥቆ ጥማትን ያረካል - እግዚአብሔር ይችላል ጥቂት ባርኮ አብልቶ ሺሁን ያበረታል - እግዚአብሔር ይችላል ተራራውን ንዶ ደልዳላ ያደርጋል - እግዚአብሔር ይችላል ደረቁን ሸለቆ በውሃ ይሞላል - እግዚአብሔር ይችላል መንፈሱን ያፈሳል ህይወትን ያድሳል - እግዚአብሔር ይችላል ሳይታክት ለሚጮህ እግዚአብሄር ይመጣል - እግዚአብሔር ይችላል ዕውርን ያበራል ሽባን ያዘልላል - እግዚአብሔር ይችላል እንቆቅልሽ ፈቶ ቋጠሮ ይበጥሳል - እግዚአብሔር ይችላል ለሞተው ማንነት ህይወትን ይሰጣል - እግዚአብሔር ይችላል ዛሬም ለሚታመን አምላኬ ይችላል - እግዚአብሔር ይችላል