Loading
Singer
አዝ፦ ይቻላል ፡ አዎን ፡ ይቻላል ይቻላል ፡ በእርግጥ ፡ ይቻላል በእግዚአብሔር ፡ ዐይን ፡ እጅግ ፡ ቀላል ፡ ነው እኛ ፡ ያቃተን ፡ ለእርሱ ፡ ምኑ ፡ ነው (፪x) ለአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፪x) ሰላሳ ፡ ስልሳ ፡ መቶ ፡ የክፉን ፡ ሃይል ፡ አጥፍቶ ለአምላክ ፡ ይቻላል ፡ ለአባት ፡ ይቻላል ከልካዩን ፡ ልከለክል ፡ አዳኙን ፡ ልናድነው ስሙ ፡ ሃያል ፡ ነው ፡ ስሙ ፡ ሃያል ፡ ነው ችሎ ፡ የሚያስችለኝ ፡ ጌታ ፡ እያለኝ ለምን ፡ ስንፍናን ፡ አወራለሁኝ አዝ፦ ለአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፪x) የቀደሙት ፡ አባቶች ፡ የእምነት ፡ ምሳሌዎች የፅድቅ ፡ አርበኞች ፡ ቆራጥ ፡ ጨካኞች መንግሥታትን ፡ ድል ፡ ነሱ ፡ ጭፍሮችን ፡ አባረሩ ድልን ፡ ዘመሩ ፡ በድል ፡ ዘመሩ አዝ፦ በአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፪x) ይቻላል ፡ አዎን ፡ ይቻላል ይቻላል ፡ በእርግጥ ፡ ይቻላል በእግዚአብሔር ፡ ዐይን ፡ እጅግ ፡ ቀላል ፡ ነው እኛ ፡ ያቃተን ፡ ለእርሱ ፡ ምኑ ፡ ነው (፪x) የእሳትን ፡ ሃይል ፡ አለፉ ፡ ክፉውን ፡ ጥሰው ፡ አለፉ በእምነት ፡ ድል ፡ ነሱ (፪x) የአናብስትን ፡ አፍ ፡ ዘጉ ፡ በእምነት ፡ እያደጉ ሄዱ ፡ ተጠጉ (፪x) አዝ፦ ይቻላል ፡ አዎን ፡ ይቻላል ይቻላል ፡ በእርግጥ ፡ ይቻላል በእግዚአብሔር ፡ ዐይን ፡ እጅግ ፡ ቀላል ፡ ነው እኛ ፡ ያቃተን ፡ ለእርሱ ፡ ምኑ ፡ ነው (፪x) ለአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፪x) ሃይልን ፡ በሚያስታጥቀን ፡ በአምላካችን ፡ ታምነን እንገባለን ፡ እንወጣለን ቃሉም ፡ እንደሚነግረን ፡ በእርሱ ፡ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን ፡ እንበልጣለን ችሎ ፡ የሚያስችለኝ ፡ ጌታ ፡ እያለኝ ለምን ፡ ስንፍናን ፡ አወራለሁኝ አዝ፦ ለአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፪x) እንወራረዳለን ፡ ለምስሉ ፡ አንሰግድም ጌታ ፡ ይረዳናል (፪x) እውነትን ፡ እንሸሽግም ፡ በወንጌል ፡ ደግሞ ፡ አናፍርም ኢየሱስ ፡ ያድናል (፪x) አዝ፦ ይቻላል ፡ አዎን ፡ ይቻላል ይቻላል ፡ በእርግጥ ፡ ይቻላል በእግዚአብሔር ፡ ዐይን ፡ እጅግ ፡ ቀላል ፡ ነው እኛ ፡ ያቃተን ፡ ለእርሱ ፡ ምኑ ፡ ነው (፪x) ለአምላኬ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል በጌታ ፡ ሁሉ ፡ ይቻላል (፬x)