Loading
Singer
ይሁን ፡ እንጂ ፡ ይብዛለት ፡ ምሥጋና ሳላቋርጥ ፡ እሰዋለሁ ፡ ገና አይደክመኝም ፡ ሁሌ ፡ አመልከዋለሁ ለሕይወቴ ፡ ትርጉሟ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው (፪x) ተሰጥቼ ፡ አመልካለሁ ፡ በፈቃዴ ፡ አመልካለሁ በመንፈሴ ፡ አመልካለሁ ፡ በእውነትም ፡ አመልካለሁ በማለዳም ፡ አመልካለሁ ፡ በቀትርም ፡ አመልካለሁ በምሽትም ፡ አመልካለሁ ፡ በሌሊትም ፡ አመልካለሁ በዝማሬም ፡ አመልካለሁ ፡ በሽብሸባም ፡ አመልካለሁ በደስታም ፡ አመልካለሁ ፡ በዕልልታም ፡ አመልካለሁ አሞጋግሼው ፡ መቼ ፡ ጨረስኩና ገና ፡ አልጠገብኩም ፡ አቅርቤ ፡ ምሥጋና ባማረ ፡ ዜማ ፡ እቀኝለታለሁ በገናዬን ፡ ይዤ ፡ ማልጄ ፡ እነሳለሁ አለብኝ ፡ ውለታው (፰x) እንዴት (፬x) ፡ እረሳለሁ እንዴት (፬x) ፡ እረሳለሁ ኧረ ፡ እንዴት (፬x) ፡ ዝም ፡ እላለሁ እንዴት (፬x) ፡ ዝም ፡ እላለሁ የተደረገልኝ ፡ ምህረት ፡ ከአሰብኩት ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው የተደረገልኝ ፡ ቸርነት ፡ ከአሰብኩት ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው የተደረገልኝ ፡ በጐነት ፡ ከአሰብኩት ፡ ከአይምሮዬ ፡ በላይ ፡ ነው ገና ፡ ከፍጥረቴ ፡ የቁጣ ፡ ልጅ ፡ ነበርኩ (፪x) ምህረት ፡ ተደርጐልኝ ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ጋር ፡ ታረኩ (፪x) ያጐበጠኝ ፡ ቀንበር ፡ ወደቀ ፡ ከላዬ (፪x) አምሮብኝ ፡ ብታዩኝ ፡ በአምላኬ ፡ ዛሬ ፡ ቀና ፡ ብዬ (፪x) በኃጥያቴ ፡ ሙታን ፡ እያለሁ ከእግዚአብሔር ፡ ምረት ፡ ተቀብያለሁ ለሆነው ፡ ነገር ፡ ምን ፡ እከፍላለሁ ቀንና ፡ ሌሊት ፡ እዘምራለሁ (፪x) አሞጋግሼው ፡ መቼ ፡ ጨረስኩና ገና ፡ አልጠገብኩም ፡ አቅርቤ ፡ ምሥጋና ባማረ ፡ ዜማ ፡ እቀኝለታለሁ በገናዬን ፡ ይዤ ፡ ማልጄ ፡ እነሳለሁ አለብኝ ፡ ውለታው (፰x) ተሰጥቼ ፡ አመልካለሁ ፡ በፈቃዴ ፡ አመልካለሁ በመንፈሴ ፡ አመልካለሁ ፡ በእውነትም ፡ አመልካለሁ በማለዳም ፡ አመልካለሁ ፡ በቀትርም ፡ አመልካለሁ በምሽትም ፡ አመልካለሁ ፡ በሌሊትም ፡ አመልካለሁ በዝማሬም ፡ አመልካለሁ ፡ በሽብሸባም ፡ አመልካለሁ በደስታም ፡ አመልካለሁ ፡ በዕልልታም ፡ አመልካለሁ