Loading
Singer
መሰዊያዬን ፡ ልስራ ፡ ከማጠኔ ፡ በፊት ከድንኳኔ ፡ ላውጣ ፡ አንተ ፡ የማትከብርበትን ፡ አዎ እንጨቴን ፡ ልረብርብ ፡ አንድደው ፡ እሳቴን መስዕዋት ፡ አድርጌ ፡ ላስቀምጠው ፡ እራሴን (፪x) አንተን ፡ ደስ ፡ ካለህ ፡ አምልኮዬ አንተን ፡ ካከበረህ ፡ ኑሮዬ ክበርልኝ ፡ ጌታዬ (፪x) ክበርበት ፡ ጌታዬ (፪x) የመኖሬ ፡ ሚስጥር ፡ የመክበሬ ፡ ጅምር አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ ፡ እግዚአብሔር (፬x) የእኔ ፡ ከፍታዬ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ ፡ ጌታዬ (፪x) የእኔ ፡ የብቻዬ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ ፡ ጌታዬ (፪x) መከበሪያዬ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ ፡ ጌታዬ (፪x) የእኔ ፡ ማረፊያዬ አንተ ፡ አይደለህም ፡ ዎይ ፡ ጌታዬ (፪x) ሰማይን ፡ በስንዝር ፡ የለካህ ምድርንም ፡ በቃልህ ፡ ያፀናህ እግዚአብሔር ፡ አንተ ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፬x) አላክብር ፡ አላምልክ የልቤ ፡ ጌታ ፡ ነህ አላርክ ፡ አላነግሥ የቤቴ ፡ ጌታ ፡ ነህ ላይ ፡ በሰማይ ፡ በዙፋንህ ፡ ሆነህ በምድር ፡ ያለውን ፡ ሁሉን ፡ ትገዛለህ የሚሳንህ ፡ የለም ፡ ሁሉን ፡ ትችላለህ እግዚአብሔር ፡ ትልቅ ፡ ነህ (፪x)