Loading
Singer
ሰው ፡ ከሆነበት ፡ አስደንጋጭ ፡ ወሬ ወየው ፡ ከሚያሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ፍሬን ፡ አሄ ሳልርበተበት ፡ ሳልል ፡ የት ፡ ልግባ ከዓይኔ ፡ ሳይወጣ ፡ የሃዘን ፡ እንባ አዝ፦ ይቤዠኛል ፡ ያልኩት ፡ ይቤዠኛል ያድነኛል ፡ ያልኩት ፡ ያድነኛል (፪x) ነፍሴ ፡ ማን ፡ አለና ፡ የቱን ፡ ለማን ፡ ስትል ድንገት ፡ ስታጣቸው ፡ ቃል ፡ የገቡላትን እጆቹን ፡ ዘርግቶ ፡ አቅፎ ፡ የተቀበላት በጣም ፡ በጭንቋ ፡ ቀን ፡ አላት ፡ የሚቤዣት (፪x) አዝ፦ ይቤዠኛል ፡ ያልኩት ፡ ይቤዠኛል ያድነኛል ፡ ያልኩት ፡ ያድነኛል (፪x) እተርፋለሁ ፡ አላልቅም ፡ አብሬ የሚያድነኝ ፡ ገብቷል ፡ በመንደሬ የሚያድነኝ ፡ ገብቷል ፡ በሰፈሬ ለኃጢአተኛው ፡ የሚመጣው ፡ ዱላ የጻድቁን ፡ ቤት ፡ አይነካምና የመንፈሱን ፡ ቤት ፡ አይነካምና እሩትን ፡ ከተቤዣት ፡ ከቡሄዝ ፡ በልጦ ለተሻለው ፡ ኪዳን ፡ ለእኔ ፡ ዋስ ፡ የሆነው ልቤን ፡ የጣልኩበት ፡ ጌታ በጭንቄ ፡ ደራሽ ፡ ነው ፡ ሚያስመካ (፪x) እተርፋለሁ ፡ አላልቅም ፡ አብሬ የሚያድነኝ ፡ ገብቷል ፡ በመንደሬ የሚያድነኝ ፡ ገብቷል ፡ በሰፈሬ ለኃጢአተኛው ፡ የሚመጣው ፡ ዱላ የጻድቁን ፡ ቤት ፡ አይነካምና የመንፈሱን ፡ ቤት ፡ አይነካምና አዝ፦ ይቤዠኛል ፡ ያልኩት ፡ ይቤዠኛል ያድነኛል ፡ ያልኩት ፡ ያድነኛል (፪x)