Loading
Singer
Updated 9/7/2026
ከአንተ ፡ ጋር ፡ የሚቆም ፡ ደፍሮ ፡ የሚወዳደር (የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ) አልተገኘም ፡ በምድር ፡ ከጫፍ ፡ ጫፍ ፡ ቢቆጠር (የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ) ሥምህ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ሥምህ ፡ ይናገራል (የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ) የትኛው ፡ ጀግና ፡ ሰው ፡ መቃብር ፡ ፈንቅሏል (የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ) (፪x) አዝ:- የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ በላይ (፫x) ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፪x) የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፬x) ብዙ ፡ ሃያላንን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ አይተናል ማኅደር ፡ ሲገለጥ ፡ ታሪክ ፡ አንብበናል የትኛው ፡ ጀግና ፡ ነው ፡ ሞትን ፡ ያሸነፈው ስንቱን ፡ ወንድ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ መቃብር ፡ የዋጠው አንተ ፡ ግን ፡ ከፍ ፡ ብለሃል ሞትና ፡ መውጊያውን ፡ ሰብረሃል ልኩራ ፡ እንጂ ፡ በአንተ ፡ እንዴት ፡ ልፈር ጌታ ፡ ነህ ፡ ታሪክ ፡ ይናገር (፪x) አዝ:- የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ በላይ (፫x) ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፪x) የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፬x) እስቲ ፡ ይናገሩ ፡ ሰማይና ፡ ምድር (የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ) የታሪክ ፡ አዋቂ ፡ ይጠራ/አምጡልኝ ፡ ምስክር (የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ) ከአንተ/ከእኔ ፡ጌታ ፡ በላይ : ሞትን ፡ ድል ፡ ያደረገ (የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ) እረ ፡ ማነው ፡ እርሱ ፡ በክብር ፡ ያረገ (የበላይ ፡ አሃሃ ፡ የበላይ) (፪x) አዝ:- የበላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ በላይ (፫x) ፡ የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፪x) የበላይ ፡ የሁሉ ፡ በላይ (፬x)