Loading
Singer
የነጻነት ፡ መዘዝ ፡ የአምልኮ ፡ ነጻነት በበጐቹ ፡ መግቢያ ፡ ትኩሎች ፡ ዘው ፡ አሉበት ሥርዓት ፡ የሌለበት ፡ ገደብ ፡ የሌለበት የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ለንግድ ፡ ጨረታ ፡ የወጣበት አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት ለአምልኮ ፡ ነጻነት ፡ ሱባኤ ፡ ተገብቶ መሰደድም ፡ ቀረ ፡ ከላይ ፡ ትዕዛዝ ፡ ወጥቶ መግቢያ ፡ በሩ ፡ ሰፋ ፡ ሰው ፡ ተግተለተለ እንክርዳዱ ፡ ስንዴ ፡ ተኩላው ፡ በግ ፡ መሰለ የድል ፡ አጥቢያ ፡ አርበኛ ፡ ዘለቀ ፡ ሆ ፡ ብሎ ውጪያዊ ፡ ምስሉን ፡ ወጉን ፡ አስተካክሎ በየጓዳው ፡ ፈላ ፡ ቤተክርስቲያን ፡ ሰሪ ራሱ ፡ ፈላጭ ፡ ቆራጭ ፡ ባለሚኒስትሪ ዶክትሪኑ ፡ በዛ ፡ መድረክ ፡ ጠበበ ጥራት ፡ ሳይሆን ፡ ብዛት ፡ ስንቱን ፡ ሰበሰበ ግርግር ፡ እንዳይሉት ፡ ወይ ፡ ዘመነ ፡ ጥፉ የአምልኮ ፡ ነጻነት ፡ ብለውት ፡ አረፉ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት ነጻነት ፡ እያሉ ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ ላወቀው ፡ ለስንቱ የነጻነት ፡ መዘዝ ፡ የአምልኮ ፡ ነጻነት በበጐቹ ፡ መግቢያ ፡ ትኩሎች ፡ ዘው ፡ አሉበት ሥርዓት ፡ የሌለበት ፡ ገደብ ፡ የሌለበት የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ለንግድ ፡ ጨረታ ፡ የወጣበት አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት መጽሃፍ ፡ ቅዱስ ፡ ኮሌጅ ፡ አጠናቅቄያለሁ ምስክር ፡ ወረቀት ፡ ቆቤንም ፡ ጭኛለሁ አንግዲህ ፡ የቀረኝ ፡ ሀያ ፡ ሰው ፡ ሰብስቤ ኪሳቸው ፡ ኪሴ ፡ ነው ፡ ለወጭ ፡ ለቀለቤ እያሉ ፡ የሚያልሙ ፡ ወንጌል ፡ ተጡዋሪዎች ዙሪያችን ፡ ፈልተዋል ፡ ሥራ ፡ ጠላቱዎች (፪x) ቀላዋጮች ፡ ብዙ ፡ ተንባዮች ፡ ለእንጐቻ መረቅ ፡ ላጠጣቸው ፡ ላበላቸው ፡ ብቻ እንደ ፡ መተተኛ ፡ እዚህ ፡ እዛ ፡ እያሉ ቅልጥም ፡ ላገኙበት ፡ ይተነብያሉ የነጻነት ፡ ውልዶች ፡ ስንቱን ፡ ያሞኛሉ በግርግር ፡ መጥተው ፡ የተቀላቀሉ ፡ የተቀላቀሉ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት ነጻነት ፡ እያሉ ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ ላወቀው ፡ ለስንቱ የነጻነት ፡ መዘዝ ፡ የአምልኮ ፡ ነጻነት በበጐቹ ፡ መግቢያ ፡ ትኩሎች ፡ ዘው ፡ አሉበት ሥርዓት ፡ የሌለበት ፡ ገደብ ፡ የሌለበት የኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ለንግድ ፡ ጨረታ ፡ የወጣበት አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት ፤ አወይ ፡ ነጻነት ራሱን ፡ የሚያዳንቅ ፡ አገልጋይ ፡ሞልቶናል ሥሙን ፡ ሲያስተዋውቅ ፡ ፎቶውን ፡ አይተናል ስብከቴ ፡ ነክቶአቸው ፡ እልፍ ፡ ሰዎች ፡ ዳኑ አጋንንቶች ፡ ወጡ ፡ ብሎ ፡ ማጋነኑ ራሱ ፡ እንዳደረገው ፡ በኃይል ፡ በጥበቡ እውቁልኝ ፡ ብሎ ፡ ሥሙን ፡ ማነብነቡ (፪x) ባለድርጂቱስ ፡ በጐ ፡ አድራጊ ፡ መሳይ በሙት ፡ ልጆች ፡ ነጋጅ ፡ ጫና ፡ ጫንቃቸው ፡ ላይ በድሀ ፡ ሥም ፡ ዞሮ ፡ ባከማቸው ፡ ሁሉ ፎቁን ፡ ገንብቶበት ፡ የሚታይ ፡ ለሁሉ ምናልባት ፡ ሲተርፈው ፡ ከርሱን ፡ ካጠገበ ትርፍራፊው ፡ ሲቀር ፡ ድሆቹን ፡ አሰበ ኦሆ ፡ ኦሆ ፡ ነጻነት ነጻነት ፡ እያሉ ሲያሞግሱሽ ፡ ዋሉ ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ ላወቀው ፡ ለስንቱ ፤ ላወቀው ፡ ለስንቱ (፪x) ጉድሽ ፡ ግን ፡ ብዛቱ ላወቀው ፡ ለስንቱ ፤ ላወቀው ፡ ለስንቱ (፪x)