Loading
Singer
አዝ፦ የአምላኩ ፡ ፈቃድ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኖ በፍጹም ፡ ነፍሱ ፡ በጌታ ፡ ታምኖ በነገር ፡ ሁሉ ፡ ሕይወቱ ፡ ረክቶ ጻድቅ ፡ ይኖራል ፡ በቃሉ ፡ ጸንቶ (፪x) የሥጋ ፡ ምኞት ፡ የዓይንም ፡ አምሮት የዓለም ፡ ፍቅር ፡ ልቡን ፡ አታልሎት በጌታ ፡ መሆን ፡ ሞኝነት ፡ መስሎት ክርስትናዉን ፡ አውልቆ ፡ ጥሎት ያንን ፡ ሰው ፡ እዩት ፡ ሲሮጥ ፡ ወደሞት አዝ፦ የአምላኩ ፡ ፈቃድ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኖ በፍጹም ፡ ነፍሱ ፡ በጌታ ፡ ታምኖ በነገር ፡ ሁሉ ፡ ሕይወቱ ፡ ረክቶ ጻድቅ ፡ ይኖራል ፡ በቃሉ ፡ ጸንቶ (፪x) የጌታን ፡ ፈቃድ ፡ ቀድሞ ፡ እየሮጠ በምኞት ፡ ባሕር ፡ ገብቶ ፡ ተዋጠ ዝናን ፡ ፍለጋ ፡ ሄደ ፡ ዋተተ እርካታን ፡ ጥሎ ፡ እየከነፈ እንደተጠማ ፡ ሳይረካ ፡ ሞተ አዝ፦ የአምላኩ ፡ ፈቃድ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኖ በፍጹም ፡ ነፍሱ ፡ በጌታ ፡ ታምኖ በነገር ፡ ሁሉ ፡ ሕይወቱ ፡ ረክቶ ጻዲቅ ፡ ይኖራል ፡ በቃሉ ፡ ጸንቶ (፪x) እንግዳው ፡ ሰው ፡ ሆይ ! የምድረበዳው የማይረባህን ፡ የምትመኘው ማንነትህን ፡ የዘነጋኸው ምኞት ፡ ኃጢአትን ፣ ኃጢአት ፡ ሞትን እንደምትወልድ ፡ እንዴት ፡ አጣኸው? አዝ፦ የአምላኩ ፡ ፈቃድ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኖ በፍጹም ፡ ነፍሱ ፡ በጌታ ፡ ታምኖ በነገር ፡ ሁሉ ፡ ሕይወቱ ፡ ረክቶ ጻድቅ ፡ ይኖራል ፡ በቃሉ ፡ ጸንቶ (፪x) የሥጋ ፡ ሩጫ ፡ ከእንግዲህ ፡ በቅቶ ከንቱ ፡ መባከን ፡ ከእንግዲህ ፡ ቀርቶ አርፈህ ፡ ተገዛ ፡ ፈቃዱን ፡ አውቀህ የጌታን ፡ ምክር ፡ ቃሎቹን ፡ ንቀህ እንዳትቀጣ ፡ ዳግም ፡ አምጸህ አዝ፦ የአምላኩ ፡ ፈቃድ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኖ በፍጹም ፡ ነፍሱ ፡ በጌታ ፡ ታምኖ በነገር ፡ ሁሉ ፡ ሕይወቱ ፡ ረክቶ ጻድቅ ፡ ይኖራል ፡ በቃሉ ፡ ጸንቶ (፪x)