Loading
Singer
የአምላኬን ፡ ቤት ፡ ጠላት ፡ ሲወርሰው ሰውም ፡ ለራሱ ፡ መኖር ፡ ሲመቸው ጠባቂው ፡ ሸሽቶ ፡ ሁሉም ፡ ሲተኛ መንጋው ፡ ሲበተን ፡ ጠፍቶ ፡ እረኛ አንጀቴን ፡ ልሰር ፡ ምግብ ፡ አልብላ ነግ ፡ ይሆናል ፡ ፍርዱ ፡ በኋላ የአምላኬ ፡ ባሮች ፡ አስኪ ፡ ተነሱ ለፈረሰው ፡ ቅጥር ፡ ኑና ፡ አልቅሱ ልመለስ ፡ ልግባ ፡ ወደ ፡ እልፍኜ ልንቃና ፡ ልማልድ ፡ ተረድቼ የደከምኩ ፡ ያረጀሁ ፡ ቢመስለም በአምላኬ ፡ እኔስ ፡ተስፋ ፡ አልቆርጥም ዓይኖቼ ፡ ፈዘው ፡ በቅጡ ፡ ሳላይ ጠላት ፡ ሲሳሳቅ ፡ በአምላኬ ፡ ቤት ፡ ላይ ከተኛሁበት ፡ ድንገት ፡ ስነቃ ቅናቱ ፡ በላኝ ፡ ሆነኝ ፡ ሰቆቃ ጉልበቴን ፡ ጠላት ፡ በልቶት ፡ ቢስቅም መውደቄን ፡ ሰምቶ ፡ ቢጠቋቆምም ወድቄ ፡ አልቀርም ፡ ደግሞ ፡ እነሳለሁ የአምላኬን ፡ ቅጥሩን ፡ አሳምራለሁ አዝ ልመለስ ማን ፡ ወድቆ ፡ ቀርቷል ፡ ሳያንሰራራ የጠላቶቹን ፡ ጡጫ ፡ እንደፈራ ባለቀ ፡ ስአት ፡ መድረስ ፡ የሚያውቀው ታማኙ ፡ አምላኬ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ነው የጠላቱን ፡ ቤት ፡ መትቶ ፡ ያፈርሳል የእርሱ ፡ የሆኑትን ፡ ጌታ ፡ ያጠራል ጸሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ ይጐበኘኛል የሱስን ፡ ይዤ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል አዝ ልመለስ በአባቴ ፡ ቤት ፡ ሸቀጡ ፡ በዝቶ ሁሉም ፡ ሊነግድ ፡ ያለውን ፡ አምጥቶ መደቡን ፡ ሰርቶ ፡ ሰው ፡ ቢመቻችም ኢየሱስ ፡ ይሄንን ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ አያይም ጌታ ፡ ጅራፉን ፡ ይዞ ፡ ይነሳል የቤቱን ፡ ጉድፍ ፡ ጠርጐ ፡ ይስወጣል የሳቀ ፡ ጠላት ፡ በተራው ፡ ያፍራል የክብሩ ፡ ቤት ፡ ግን ፡ ገና ፡ ያበራል አዝ ልመለስ