Loading
Singer
የአድናቆት ፡ ቀን ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ለወደደን የሚገባው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ እውነቱን ፡ እንወቅ ፡ ጠንቅቀን ጀብዱው ፡ ገድሉ ፡ የሚወራለት ጭፍራ ፡ አለቃው ፡ የሚስግዱለት እግዚአብሔር ፡ ምሥጉን ፡ ሥም ፡ ያለው አድናቆቱም ፡ ምሥጋናውም ፡ መገረሙም ፡ ለእርሱ ፡ ሥም ፡ ነው ማነው ፡ ፍጥረትን ፡ የሰራ ፡ ሰማይ ፡ ምድርን ፡ የቀየሰው ማነው ፡ በአፍንጫው ፡ እፍ ፡ ያለ ፡ የሕይወትን ፡ እስትንፋስ ፡ ለሰው ማነው ፡ ነፋስን ፡ አንፋሹ ፡ የእሳት ፡ የውሃው ፡ አለቃ ማነው ፡ አዛዥ ፡ የጸሀይዋ ፡ ማነው ፡ አዛዥ ፡ የጨረቃ ማነው ፡ የምድርን ፡ ዳርቻ ፡ በእጆቹ ፡ መዳፍ ፡ ያኖረ ማነ ፡ ፈርዖንን ፡ በዝቅጠት ፡ በውኃ ፡ በታች ፡ ያስቀረ ማነው ፡ ከፍታን ፡ የሚያዘው ፡ ዝቅታም ፡ የሚያረግድለት ማነው ፡ ብድራትን ፡ መላሽ ፡ ከቅርብ ፡ ወይም ፡ ከርቀት እግዚአብሔር (፬x) ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር አንተ ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ ክብር (፫x) አለቆች ፡ የምድር ፡ ፈርጆች ፡ ጐልማሶች ፡ ቆነጃጅቶች እሳትና ፡ በረዶ ፡ አመዳይ ፡ ጨምሮም ፡ ውርጮች ተራሮችና ፡ ኮረብቶች ፡ ፍሬ ፡ የሚያፈሩ ፡ ዝግቦች በቃሉ ፡ ሲንቀጠቀጡ ፡ እዩት ፡ ሲያደንቁት ፡ ፍጥረቶች ማነው ፡ የዋሁን ፡ ታዳጊ ፡ መመኪያ ፡ ለቅዱሳኑ ማነው ፡ ቅን ፡ ፈራጅ ፡ መጠጊያ ፡ ለሥሙ ፡ ታምነው ፡ ለጸኑ ማነው፡ ጉሙን ፡ የሚበትን ፡ የአንበሳን ፡ መንጋጋ ፡ ያደቀቀ ማነው ፡ ወጥመድን ፡ ሰባሪ ፡ ህዝቡን ፡ ከግዞት ፡ የጠበቀ እግዚአብሔር (፬x) ቅዱስ ፡ ቅዱስ ፡ እግዚአብሔር አንተ ፡ ብቻ ፡ አንተ ፡ ክብር (፫x)