Loading
Singer
የአደባባይ ፡ ሰው ፡ ሆነህ በየማዕዘኑ ፡ ላይ ፡ ቆመህ ሰውን ፡ አይተህ ፡ በሰው ፡ ታይተህ (፪x) በስወር ፡ አይቶ ፡ በግልጥ ፡ የሚከፍልህን በከፍታ ፡ ላይ ፡ የሚያስኬድህን ረስተህ ፡ የለም ፡ ወይ ፡ አሳዳጊ ፡ ጌታህን በስውር ፡ የሚቀመጡ ጌታቸውን ፡ የሚያደምጡ የሕይወትን ፡ ቃል ፡ የሚያመጡ (፪x) ሰውን ፡ ለማነጽ ፡ ነቅተው ፡ የሚታጠቁ ለበጐ ፡ ሥራ ፡ ሁሉ ፡ የሚበቁ ምስጉኖች ፡ ናቸው ፡ መማለድን ፡ የሚያዉቁ ከእግዚአብሔር ፡ የተላከ እርሱ ፡ ነው ፡ የተባረከ ቃሉን ፡ ብቻ ፡ እየሰበከ (፪x) አንተንስ ፡ ማነው ፡ አስነስቶ ፡ የላከህ በፍጻሜው ፡ ላይ ፡ ትጠየቃለህ እንደ ፡ ሥራህም ፡ ያኔ ፡ ትከፈላለህ ሥራህ ፡ ድካምህ ፡ ብዙ ፡ ነው አንተነትህን ፡ ያጐላው ጌታ ፡ እንዳይታይ ፡ የጋረደው (፪x) እስኪ ፡ በእውነት ፡ መርምረው ፡ ሕይወትህን መፀለይ ፡ ትተህ ፡ መራቆትህን ኢየሱስን ፡ ጋርደህ ፡ አንተ ፡ መታየትህን ስማው ፡ ኢየሱስ ፡ ይመክርሃል "ተው ፣ እረፍ ፣ ፀልይ" ፡ ይልሃል ከእግሮቹ ፡ ሥር ፡ ሥጋህን ፡ ጣል (፪x) ያን ፡ ጊዜ ፡ ጌታ ፡ በሰገነት ፡ ላይ ፡ ወጥቶ ለዓለም ፡ ይታያል ፡ ብርሃኑ ፡ በርቶ ሕይወት ፡ ይበዛል ፡ የስንዴው ፡ ቅንጣት ፡ ሞቶ