Loading
ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ወደማን ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ (፪x) ድምጽህን ፡ ሰምቼ ፡ አንዴ ፡ ተደላድያለሁ የሕይወት ፡ ቃል ፡ አለ ፡ በአንተ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ ሰለቸኝ ፡ ደከመኝ ፡ አታውቅ ፡ እኔ ፡ አይቼሃለሁ ታዲያ ፡ ከእቅፍህ ፡ ወዴት ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ አባት ፡ ቢሉት ፡ የደረሰላቸው ፍቅር ፡ ሚሉት ፡ የቀመሱት ፡ ናቸው ተስፋ ፡ ጠፍቶ ፡ ተስፋ ፡ የሆናቸው በተዐምራት ፡ በድንቅ ፡ የመራቸው አመስግኖ ፡ አይጠግብም ፡ ልባቸው (፪x) ክበር ፡ ብሎ ፡ ንገሥ ፡ ብሎ (አሜን) ልዩ ፡ ብሎ ፡ አይጠግብም ፡ ልባቸው (፪x) ያየሁትን ፡ የሰማሁትን (የሰማሁትን) እናገራለሁ ፡ ያረፍኩበትን (ያረፍኩበትን) (፪x) ሞተና ፡ በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ተነሳና ሞተና ፡ በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ተነሳና ነፃ ፡ አደረገኝ ፡ ዕዳዬን ፡ ከፈለና ቀኑን ፡ ሙሉ ፡ በፍቅርህ ፡ በቤትህ ፡ እኖራለሁ (፪x) በሚያስተማምነው ፡ ክንድህ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ አርፌአለሁ በውኃ ፡ ዳር ፡ እንደአለች ፡ ተክል ፡ ፍሬያማ ፡ ሆኛለሁ የረገጥኩት ፡ ምድር ፡ በአንተ ፡ ሲገዛ ፡ አይቻለሁ ስምህን ፡ ጠርቼ ፡ ጌታ ፡ መቼ ፡ አስነካለሁ ያየሁትን ፡ የሰማሁትን (የሰማሁትን) እናገራለሁ ፡ ያረፍኩበትን (ያረፍኩበትን) (፪x) ሞተና ፡ በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ተነሳና ሞተና ፡ በሶስተኛው ፡ ቀን ፡ ተነሳና ነፃ ፡ አደረገኝ ፡ ዕዳዬን ፡ ከፈለና
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.