Loading
Singer
ዛሬ ፡ ብዬ ፡ የጠራሁት ፡ ቀን ፡ ትላንት ፡ ተብሎ ፡ አልፎ ፡ ሲወራ ብርቱ ፡ መስሎ ፡ የታየው ፡ ሰው ፡ ለቀብሩ ፡ ሞቱ ፡ ሲሰማ ፍጥረት ፡ ቦታውን ፡ ለቆ የቆመው ፡ ደግሞ ፡ ወድቆ ቀና ፡ ስል ፡ ኢየሱስ ፡ ያው ፡ ነው ቀና ፡ ስል ፡ ጌታዬ ፡ ያው ፡ ነው ፡ ነው ይባላ ፡ ቀና ፡ ይባላ ፡ ቀና ብርቱ ፡ የሆነ ፡ አምላክ ፡ አለና ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ ዘላለም ፡ ሚኖር ፡ አለ ፡ በሰማይ አለሁ ፡ አለሁ ፡ ያለው ፡ ሰው ድንገት ፡ ጉልበት ፡ ሲከዳው ሁሉን ፡ ዘመን ፡ በቃ ፡ ሲለው እንደ ፡ ጥላ ፡ ሲያሳልፈው ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ ያው ግርማዊነቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገም ፡ ያው ይባላ ፡ ቀና ፡ ይባላ ፡ ቀና ብርቱ ፡ የሆነ ፡ አምላክ ፡ አለና ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ ዘላለም ፡ ሚኖር ፡ አለ ፡ በሰማይ አደራ ፡ የተባለው ፡ ለአደራው ፡ ሳይበቃ ዓይን ፡ የተጣለበት ፡ ከስፍራው ፡ ሲታጣ ማነው ፡ ጽኑ ፡ ብዬ ፡ ስጠይቅ ፡ ጥያቄ ቃሉ ፡ እንዲህ ፡ እያለ ፡ ፈሰሰ ፡ ከውስጤ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ትላንትናም ፡ ዛሬም ፡ እስከ ፡ ለዘላለም ፡ ያው ፡ ነው አንቱ ፡ ተብሎ ፡ ሚወራለት ጐንበስ ፡ ቀና ፡ ሚባልለት እንዲያው ፡ ሲቀር ፡ በትዝታ አንደ ፡ እለ ፡ ግን ፡ ሕያው ፡ ጌታ ፡ ንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ዛሬም ፡ ያው ግርማዊነቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ነገም ፡ ያው ይባላ ፡ ቀና ፡ ይባላ ፡ ቀና ብርቱ ፡ የሆነ ፡ አምላክ ፡ አለና ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ ፡ ይታይ ፡ ወደ ፡ ላይ ዘላለም ፡ ሚኖር ፡ አለ ፡ በሰማይ