Loading
Singer
እንዲህ ፡ የምሆነው ፡ በዚህ ፡ ጉብዝናዬ ያረፈበት ፡ ዓይኔ ፡ የወደደው ፡ ልቤ በኢየሱስ ፡ ቁንጅና ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ያለው ፡ ሀሳቤ ያረፈበት ፡ ዓይኔ ፡ የወደደው ፡ ቀልቤ በኢየሱስ ፡ ቁንጅና ፡ ላይ ፡ ነው ፡ ያለው ፡ ሃሳቤ ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ ይየው ፡ ይየው ፡ ጌታን ፡ ይየው አንዴ ፡ ቀምሶ ፡ ካጣጣመው ፡ ሌላ ፡ አያሰኘው ሌላውን ፡ ላልወድ ፡ ሌላዉን ፡ ላልሻ በሌላ ፡ ላልታለል ፡ ሌላዉን ፡ ላልሻ ተማርኬያለሁ ፡ እስከመጨረሻ (፪x) አመልከዋለሁ ፡ እስከመጨረሻ (፪x) ያገር ፡ ቆንጆ ፡ ነኝ ፡ ባዩ ፡ ከውዴ ፡ ሲተያዩ ያመረ ፡ መሳይ ፡ ዉበቱ ፡ ዉዴ ፡ ይበልጠዋል ፡ በስንቱ ያገር ፡ ቆንጆ ፡ ነኝ ፡ ባዩ ፡ ከየሱስ ፡ ሲተያዩ ያመረ ፡ መሳይ ፡ ዉበት ፡ ዉዴ ፡ በዛበት ፡ በስንቱ ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ ይየዉ ፡ ይየው ፡ ጌታን ፡ ይየዉ አንዴ ፡ ቀምሶ ፡ ካጣጣመዉ ፡ ሌላ ፡ አያሰኘዉ እንዲህ ፡ የምሆነው (፪x) የኢየሱስ ፡ ውበቱ ፡ ከሁሉ ፡ በልጦብኝ ፡ ነው በዚህ ፡ ጉብዝናዬ ፡ ለዓለም ፡ ማልገዛው ያዘጋጀው ፡ ክብር ፡ ከዓለም ፡ በልጦብኝ ፡ ነው (፪x) አገር ፡ ሁሉ ፡ ያደነቀው ፡ ሰዓሊው ፡ የሳለው አይ ፡ ሞኙ ፡ መች ፡ ገባው ፡ የኔን ፡ ቆንጆን ፡ አላየው አገር ፡ ሁሉ ፡ ያደነቀው ፡ ሰዓሊው ፡ የሳለው አይ ፡ ሞኙ ፡ መች ፡ ገባው ፡ ኢየሱሴን ፡ አላየው ፍጥረት ፡ በሙሉ ፡ ይየዉ ፡ ይየው ፡ ጌታን ፡ ይየዉ አንዴ ፡ ቀምሶ ፡ ካጣጣመዉ ፡ ሌላ ፡ አያሰኘዉ ውበትን ፡ ላልፈልግ ፡ ዓለምን ፡ ላልሻ በዓለም ፡ ላልታለል ፡ ውበትን ፡ ላልሻ አግኘቸዋለሁ ፡ እስከመጨረሻ (፪x) ወርሼዋለሁ ፡ እስከመጨረሻ (፪x) እንዲህ ፡ የምሆነው (፪x) የኢየሱስ ፡ ውበቱ ፡ ከሁሉ ፡ በልጦብኝ ፡ ነው በዚህ ፡ ጉብዝናዬ ፡ ለዓለም ፡ ማልገዛው ያዘጋጀው ፡ ክብር ፡ ከዓለም ፡ በልጦብኝ ፡ ነው (፬x)