Loading
Singer
አዝ፦ የተሰጠኝ ፡ ኪዳን ፡ እውነት ፡ ነው ፡ ተስፋዬ ስጋት ፡ የለብኝም ፡ እኔስ ፡ ይከዳኛል ፡ ብዬ ቃሌ ፡ እርሱን ፡ ይጣፍጠው ፡ ይግባ ፡ ከመቅደሱ አመሰግናለሁ ፡ ክብር ፡ ንጉሡ (፪x) በኢየሱስ ፡ ታመኑ ፡ ዛሬም ፡ እላለሁ ዘንዶው ፡ ሲያዋርድ ፡ ሲጥል ፡ ስላየሁኝ ላዘነው ፡ መጽናኛ ፡ ላለቀሰው ፡ ደስታ አስታዋሽ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ቀድሞም ፡ ለተረሳ (፪x) አዝ፦ የተሰጠኝ ፡ ኪዳን ፡ እውነት ፡ ነው ፡ ተስፋዬ ስጋት ፡ የለብኝም ፡ እኔስ ፡ ይከዳኛል ፡ ብዬ ቃሌ ፡ እርሱን ፡ ይጣፍጠው ፡ ይግባ ፡ ከመቅደሱ አመሰግናለሁ ፡ ክብር ፡ ንጉሡ ኢየሱስ ፡ በቂ ፡ ነው ፡ ከምንም ፡ በላይ ለነፍሴ ፡ መጽናኛ ፡ ሆኗል ፡ ኤልሻዳይ አታዋኪ ፡ ነፍሴ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኪ ለአንቺ ፡ የሰራልሽ ፡ የለውም ፡ ተተኪ (፪x) አዝ፦ የተሰጠኝ ፡ ኪዳን ፡ እውነት ፡ ነው ፡ ተስፋዬ ስጋት ፡ የለብኝም ፡ እኔስ ፡ ይከዳኛል ፡ ብዬ ቃሌ ፡ እርሱን ፡ ይጣፍጠው ፡ ይግባ ፡ ከመቅደሱ አመሰግናለሁ ፡ ክብር ፡ ንጉሡ የጨለማው ፡ ወራት ፡ አለፈ ፡ እንደዋቃ ቃል ፡ ይዤ ፡ ስወጣ ፡ በነነ ፡ እንደ ፡ ጤዛ ነፍሴም ፡ አስታወሰኝ ፡ ያደረገላትን ወደ ፡ እርሱ ፡ ቀረበ ፡ ልሰዋ ፡ አምልኮን (፪x) አዝ፦ የተሰጠኝ ፡ ኪዳን ፡ እውነት ፡ ነው ፡ ተስፋዬ ስጋት ፡ የለብኝም ፡ እኔስ ፡ ይከዳኛል ፡ ብዬ ቃሌ ፡ እርሱን ፡ ይጣፍጠው ፡ ይግባ ፡ ከመቅደሱ አመሰግናለሁ ፡ ክብር ፡ ንጉሡ