Loading
Singer
ተክሎ ፡ መሄድ ፡ የአንተን ፡ ፍለጋ ምነኛ ፡ መልካም ፡ ነው ፡ ቢበዛልኝ ፡ ፀጋ አስከብሬህ ፡ ልለፍ ፡ እንደ ፡ አባቶቼ ዓለም ፡ እና ፡ ትርፏን ፡ ሁሉን ፡ ንቄ ፡ ትቼ (፪x) አዝ፦ ክርስትናን ፡ መኖር ፡ ዋጋ ፡ በመክፈል ፡ ነው ግን ፡ የለብስኩት ፡ ሥጋ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነው ከጐኔ ፡ በመቆም ፡ ካላበረታኸኝ ታውቃለህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ (፪x) ዘወትር ፡ በፀሎት ፡ በፊትህ ፡ ልደፋ በውስጤ ፡ ያኖርከው ፡ እሳቱ ፡ እንዳይጠፋ ገና ፡ ላገልግልህ ፡ በኃይል ፡ ተሞልቼ ጉብዝናዬን ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ሰጥቼ (፪x) አዝ፦ ክርስትናን ፡ መኖር ፡ ዋጋ ፡ በመክፈል ፡ ነው ግን ፡ የለብስኩት ፡ ሥጋ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነው ከጐኔ ፡ በመቆም ፡ ካላበረታኸኝ ታውቃለህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ (፪x) ባላደራነቴን ፡ ችላ ፡ እንዳልለው የወንጌልን ፡ ዕንቁ ፡ ለራ ፡ እንዳልጥለው ታማኝ ፡ አድርገህ ፡ ቆጥረህ ፡ በቤትህ ፡ የሾምከኝ ከፈተናዎቼ ፡ ፀጋህ ፡ ያሾልከኝ/ያስመልጠኝ (፪x) ሰርክ ፡ እናይሳነኝ ፡ መንጋህን ፡ በመገብ በሸክላ ፡ ዕቃ ፡ ውስጥ ፡ የከበረ ፡ መዝገብ ያስቀመጥክ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ እንደ ፡ ኃይልህ ፡ ብዛት እስከ ፡ መጨረሻው ፡ ሕይወቴን ፡ አግዛት (፪x) አዝ፦ ክርስትናን ፡ መኖር ፡ ዋጋ ፡ በመክፈል ፡ ነው ግን ፡ የለብስኩት ፡ ሥጋ ፡ እጅግ ፡ ደካማ ፡ ነው ከጐኔ ፡ በመቆም ፡ ካላበረታኸኝ ታውቃለህ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እኔ ፡ ደካማ ፡ ነኝ (፪x)