Loading
Singer
ምሥጋና ፡ የተጋውን ፡ እግዚአብሔርን ፡ እጠራዋለሁኝ መቅደሱን ፡ በዕልልታዪ ፡ እበዝማሬ ፡ እሞላዋለሁ ይኸው ፡ ምሥጋናው ፡ ይኸው ፡ ዝማሬው ይኸው ፡ ዕልልታው ፡ ስለሚገባው (፪x) የሚሰዋልኝ ፡ ለእኔ ፡ ምሥጋና እርሱ ፡ ያከብረኛል ፡ ብሎኛልና ሞላ ፡ ጐደለ ፡ ሳልል ፡ እሰዋለሁ በሙሉ ፡ ኃይሌ ፡ አመልከዋለሁ አመልከዋለሁ (፬x) ነገ ፡ ለራሱ ፡ ይጨነቅ ፡ ይጨነቅ ፡ እንጂ እኔስ ፡ አርፌ ፡ እኖራለሁ ፡ በአምላኬ ፡ እጅ ነገ ፡ ለራሱ ፡ ይጨነቅ ፡ ይጨነቅ ፡ እንጂ እኔስ ፡ አርፌ ፡ እኖራለሁ ፡ በአምላኬ ፡ እጅ አዝ፦ ነገሬን ፡ በሚያውቅልኝ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ ትላንትን ፡ ያሻገረኝ ፡ ለነገም ፡ አምነዋለሁ (፪x) ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል ያኖረኛል ፡ ገና ፡ ያሳየኛል ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል ጠላት ፡ ዙሪያዬ ፡ ሲዞር ፡ ይውላል አባባ ፡ ቅጥሬን ፡ በእሳት ፡ ቀጥሮታል አያገነኝም ፡ ሌት ፡ ቀን ፡ ቢለፋ የሚጠብቀኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አያንቀላፋም አያንቀላፋም (፬x) አዝ፦ ነገሬን ፡ በሚያውቅልኝ ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ ትላንትን ፡ ያሻገረኝ ፡ ለነገም ፡ አምነዋለሁ (፪x) ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል ያኖረኛል ፡ ገና ፡ ያሳየኛል ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል ሃማ ፡ በቅናት ፡ ሞትን ፡ ደግሶ ለመርዶኪዮስ ፡ ጉድጓድ ፡ ተምሶ መቼ ፡ ለጠላት ፡ ታልፎ ፡ ተሰጠ አምላኩ ፡ ደርሶ ፡ ነገሩ ፡ ተገለበጠ ተገለበጠ (፬x) ሰምቼ ፡ ነበረ ፡ በጆሮዬ ሁሉን ፡ ቻይ ፡ እንደሆንክ ፡ አባብዬ ዛሬም ፡ ዐይኔ ፡ አይታሃለች ነፍሴ ፡ ታመሰግናለች እንደሰማሁ ፡ እንዲሁ ፡ አየሁ (፫x) ፡ ሆ እንደሰማሁ ፡ እንዲሁ ፡ አየሁ (፫x) ፡ ሆ ከዘለዓለም ፡ ፍርድ ፡ ከሞት ፡ ፍርሃት በደም ፡ ኪዳን ፡ ነው ፡ ነፍሴን ፡ የዋጃት በላይ ፡ በረከት ፡ አንዴ ፡ ባርኮኛል ኢየሱስ ፡ አለልኝ ፡ ኧረ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ ያሰጋኛል ምን ፡ ያሰጋኛል (፬x) አዝ፦ ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል ያኖረኛል ፡ ገና ፡ ያሳየኛል ያኖረኛል ፡ እርሱ ፡ ያሳየኛል